Get Mystery Box with random crypto!

ሁሉ ነገሩ ጥሎ ወደ ነቢያችን ﷺ የሄደው ታላቅ ሰው የጆንያው ባለቤት የአብደላህ_ዙል_ቢጃደ | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

ሁሉ ነገሩ ጥሎ ወደ ነቢያችን ﷺ የሄደው ታላቅ ሰው የጆንያው ባለቤት የአብደላህ_ዙል_ቢጃደይን

#የአብደላህ_ዙል_ቢጃደይን(ረ.ዐ) የህይወት ታሪክ
እስልምናን በመቀበሉ ብቻ የለበሰውን ልብስ እንኳን ሳይቀር በአጎቱ ሀብት ንብረቱን ተቀምቶ ጆንያ ለብሶ የናፈቃቸውን ነቢዩን ﷺ ለማግኘት ጉዞውን ወደ መዲና አደረገ ልክ መዲና ሲደርስ የነቢዩን ﷺ ቤት በር ላይ ቆሞ የእነርሱን ከቤት መውጣት በናፍቆት ይጠባበቅ ጀመር ነቢዩ ﷺ ከቤት ሲወጡ ባየ ጊዜ የደስታ እንባው ጉንጩ ላይ መፍሰስ ጀመረ የናፈቃቸውን ወዳጆቹን እና
ነቢዩ ሶላት አሰግደው እንደጨረሱ እንደ ልምዳቸው ቆሙ እና ማን ሰገደ ማን ቀረ እያሉ የባልደረቦቻቸውን ፊት ማስተዋል ጀመሩ፦

ከዛ ይሄንን ወጣት አዩት ከየት ነው የመጣህ አንተ ወጣት ብለው ጠየቁት እርሱም ከሙዘይና ጎሳ ነው ሸሽቼ የመጣሁት አሏቸው፦ ነብዩ ስምህ ማነው አሉት አብዱል_ኡዛ(የኡዛ_ባርያ) እባላለሁ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተገርመው አዩት እና ይሄ የለበስከው ጆንያ ምንድነው ልብስ የለህም ብለው ጠየቁት፦

እርሱም አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ አጎቴ በእርሶ መስለሜን ባወቀ ጊዜ ያለኝን ንብረቴን ሁሉ ቀማኝ ከእነዚህ ጆንያዎች ውጪ ምንም አላገኘሁም አንተን ለመገናኘት ስል ላይ እና ታች አስሬ ወደ አንተ መጣሁ የአላህ መልእክተኛ አሏቸው፦

ነቢዩ ﷺ ይህንን አደረክ እንዴ አንተ ለአላህ እና መልእክተኛው ስትል ንብረትህን ጥለህ መጣህ ? አላህ በእነዚህ ሁለት ጆንያዎች ልብስ ይስጥህ ጀነት ውስጥ የፈለከውን እየበላህ የፈለከውን ለብሰህ ኑር በጀነት ውስጥ አንተ ከአሁን በኋላ #አብዱል_ኡዛ አይደለህም #ዙል_ቢጃደይን ነህ የጆንያዎች ባለቤት ነው ስምህ ።

ኡላሞች ይሄ ሰው የውመል ቂያማ መክሉቃታ በአላህ ፊት በቆመበት ፊት ይጠራል አንተ ዙል ቢጃደይን ውጣ ወደ አላህ ይባላል ።

ዙል ቢጃደይን ንብረቱን ሁሉ ነገሩን ትቶ ወደ ነቢዩ ﷺሸሸ እራቁቱን እሳቸው ጋር ተገናኘ አህለ ሶፋ የሚባሉ ነቢዩ ﷺሶሃባዎች ደሀዎች ከነብዩ ቤት ጀርባ የሚኖሩ ሰዎች አሉ ከነሱ ጋር መኖር ጀመረ ይሄ ሶሃባ ።

አብዱል ኡዛ የዛሬው አድሱ ስሙ አብደላህ ዙል ቢጃደይን ይባላል አብደላህ ከሰለመ በኋላ የአላህ ሱብሃናሁ ወተአላ ትልቅ ባርያ ሆነ ከኢባዳዎቹ ውስጥ በጣም ዱዓ እና ዚክር ያበዛ ነበር፦ ተመላሹ ተፀፃቹ ብለው ነበር ስሙን የሚጠሩት ሌላው ባህሪው ቁርአን መቅራት በጣም ያበዛ ነበር ።

ከችግር ጋር ምቾት አለ ። ከፈተናዎች በኃላ ኸይር ነገር ይመጣል ።

65፦7 አላህ ከችግር በኋላ ምቾትን በእርግጥ ያደርጋል፡፡
94፦5 ከችግርም ጋር ምቾት አልለ፡፡

ኢብኑ አህመድ


https://t.me/joinchat/RXYpviFTL70OQdu2