Get Mystery Box with random crypto!

የስልጤ፣ጉራጌና ሐዲያ ዞኖችን ከሲዳማ ክልል ጋር በማቀናጀት የሚሰጥ የንፅፅር ሃይማኖት ትምሕርት ሲ | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

የስልጤ፣ጉራጌና ሐዲያ ዞኖችን ከሲዳማ ክልል ጋር በማቀናጀት የሚሰጥ የንፅፅር ሃይማኖት ትምሕርት ሲሆን ስልጠናው በአጠቃላይ በሶስት ወራት ውስጥ በአሏህ ﷻ ፍቃድ የሚጠናቀቅ ይሆናል። በዚህ ኮርስ ተሳታፊ ለመኾን የምትፈልጉ የአካባቢው ተወላጆችና ነዋሪዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች ካሟሉ መመዝገብ ይችላሉ፦
.
1/ መሠረታዊ የእስልምና ሀይማኖት እውቀት ያለው/ላት ሊሆን ይገባል። ይኸውም ከቁርአን ማኽተም ጀምሮ እስከ መግቢያ ኪታቦች በመጠኑም ቢሆን የቀራ/ች ሊሆን ያስፈልጋል።
.
2/ ከተቻለ ሁለቱን ቋንቋዎች የሚረዳ/የምትረዳ (አረብኛና እንግሊዝኛ) ካልሆነ ቢያንስ አንደኛውን ቋንቋ በሚገባ ማንበብና መረዳት የሚችል/ትችል መሆን ይኖርበታል።
.
3/ ትምህርቱን ሙሉ ለሙሉ ለመጨረስ እንደሁም ትምህርቱ የሚያስፈልገውን ጥናት፣ ውይይት ጊዜ ሰጥቶ ለማካሄድ ዝግጁ የሆነ/ች መሆን ይኖርባቸዋል።

4/ ከስልጠናው በዃላ በአከባቢው/ዋ የሚገኙ ወንድምና እህቶችን በዳዕዋው ለማገዝ ፈቃደኛ የሆነ/ች።

ለመመዝገብ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን በቴሌ ግራም ላይ ያናግሩን

t.me/hidden_life_hi

t.me/Nesriyaaa

t.me/zhara_temary