Get Mystery Box with random crypto!

ፖለቲከኛና ጋዜጠኛ ለሚዲያ ፍጆታ የሚያውለው ማስመሰል እንጂ እምነታችን የሚፈቅደው ተግባር አይደለም | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

ፖለቲከኛና ጋዜጠኛ ለሚዲያ ፍጆታ የሚያውለው ማስመሰል እንጂ እምነታችን የሚፈቅደው ተግባር አይደለም!

አዎ ይሄ "አንድነት" ነው። ኢስላምን በመናድ የእምነትን አጥር በማፍረስ የሚፈፀም ዝብርቅርቅ ህብረት። በዚህ አይነት ተግባር ሙስሊሙም ክርስቲያኑም አይጠቀምም። አብሮ የመኖር እሴትም አይዳብርም። አገርም አታተርፍም። ፖለቲከኛና ጋዜጠኛ ለሚዲያ ፍጆታ የሚሰራው የማስመሰል ስራ ሲኖር የዋሃንን ለዚህ አይነት ጥፋት ያሰልፋል። ደግሞ "ሰላም ይህ ነው" ይባልልናል። እንዲያውም እውነቱን እንናገር ከተባለ ሃይማኖት በዚህ መልኩ የፖለቲከኛና የጋዜጠኛ መጫወቻ ከሆነ ወዲህ ነው ይበልጥ ሰላም ያጣነው። ሁሉም የእምነቱን አጥር ጠብቆ ሰላም ማስከበር እንደሚቻል ያልተረዳ አካል ስለ ሰላም የማውራት አቅም ላይ ገና አልደረሰም።

እንዲህ አይነቱ ኢስላም የማይፈቅደውን ተግባር የምንኮንነው ሰላምና መቻቻል ስለማንፈልግ አይደለም። በፍፁም! እንዲያውም ከሰላም ይበልጥ አትራፊዎቹ እኛ፣ በሰላም መጥፋት ይበልጥ ተጎጂዎቹም እኛ ነን ብለን እናምናለን። ታዲያ እንዲህ አይነቱን የማደበላለቅ አካሄድ የምንቃወመው ሃይማኖታችን ጋር የሚጋጭ ተግባር ስለሆነ ነው።

ስለዚህ የህዝቡን ሰላም ለማስጠበቅና በመልካም ተባብሮ የመኖር እሴት ለማጎልበት አንድ ሺ አንድ አማራጭ መጠቀም ሲቻል ሁሌ በአል እየጠበቁ ሙስሊሙ ታቦት እንዲሸኝ፣ መስቀል እንዲያከብር ማድረግ ወይም መጣራት ወይም ደግሞ እንዲህ አይነቱን ተግባር የመቻቻል ማሳያ አድርጎ መሳል የራሱ አፍራሽ ገፅታ አለው። ምክንያቱም እንዲህ አይነቱ ተግባር በኢስላም በእጅጉ የተኮነነ ስለሆነ እምነቱ የሚጠይቃቸውን የማንቃት ስራ የሚሰሩ ሙስሊሞችን በጠርዘኝነት እንዲሳሉ ቀዳዳ ይከፍታልና።

ዛሬም ከአንዳንዶች እያስተዋልን ያለነው ይሄንኑ ነው።
ከዚህ ይልቅ ዜጎች አብረው ለሰላም እንዲተጉ፣ በችግራቸው እንዲረዳዱ፣ ከተንኳሽና ፀብ ጫሪ ተግባራት እንዲታቀቡ፣ በየቤተ እምነቱ አድፍጠው ወጣቱን ለግጭት እያነሳሱ ያሉ ሰባኪዎች ስርአት እንዲይዙ፣ በአል በመጣ ቁጥር እየተከሰቱ ላሉ ግጭቶች ገፊ ምክንያቶች ላይ ትኩረት ተደርጎ ከምንጫቸው እዲደርቁ ማድረግ ላይ መስራት ነው የሚበጀው። እንጂ ባዶ መሸነጋገል፣ መሸዋወድ የትም አያደርሰንም።

@ኢብኑ ሙነወር