Get Mystery Box with random crypto!

ክርስትና ሃይማኖት ላይ የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ተሰርተው የተለያዩ ለአምልኮ የሚጠቀሙዋቸው ነገ | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

ክርስትና ሃይማኖት ላይ የተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ተሰርተው የተለያዩ ለአምልኮ የሚጠቀሙዋቸው ነገሮች እንዳሉ ተናግሪያለው ። እሥልምና ሃይማኖት ላይ ግን ይህንን አላየውም ። አምልኮ የሚገባው ለአላህ ብቻ እንደሆነ ነው የተረዳው ለምሳሌ ብንመለከት ሱረቱል ጂን ቁጥር 18 ላይ መስጂዶች የአላህ ብቻ ናቸው በመሆኑም ከአላህ ጋር (ዉጪ) ማንንም አታምልኩ ነው የሚለው አምልኮ የሚገባው ለአላህ ብቻ እንደሆነ ተረድቻለዉ ሰለዚህ ወደ እሥልምና ሃይማኖት እንድገባ አድርጎኛል ማለት ነው ። በመቀጠል ደግሞ እኔ የክርስትና እምነት እያለዉ እሥልምና ሃይማኖትን አድርጌ የማስበው አዲስ ነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ያመጣው እምነት ነው ብየ ነበር የማምነው ከክርስትና ሃይማኖት በኋላ የተቋቋመና አዲስ እምነት ነው ብየም አስብ ነበር ።

ከክርስትና እምነት በኋላ የተቋቋመው ብየ ማስረጃ የማቀርብበት የሆነው አመተ ሂጅራ አቆጣጠርን መሰረት በማድረግ ነው ። አመተ ሂጅራ አቆጣጠር የሚጀምረው እሥልምና በተጀመረበት ዘመን ነው ብየ ነበር የማምነው ። እንዲህ ብየ የማምነው እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙዎቹ ክርስቲያኖች እሥልምና ሃይማኖት ከክርስትና ሃይማኖት በኋላ የተቋቋመ አዲስ እምነት ለመሆኑ እንደ ማስረጃ የሚጠቀሙት አመተሂጅራን ስለሆነ ነው ። ለማንሳት የፈለኩት ዳሩ ግን አመተ ሂጅራ አቆጣጠር መጀመር እና እሥልምና እምነት መጀመር በአንድ ላይ የተጀመሩ ነገሮች አለመሆናቸውን ተረድቻለው ።

አመቱ ሂጅራ አቆጣጠር የሚጀመረው ነቢያችን ሙሐመድ ﷺ በተላኩ ከ13 አመት በኋላ ነው ሂጅራ በራሱ ትርጉሜ ስደት ማለት ነው ። ከመካ ወደ መዲና ካደረጉት ስደት ከዛ ጊዜ ጀምሮ ነው አመተሂጅራ የሚጀምረው ። እሥልምና ሃይማኖት ግን የሚጀምረው ከአባታችን አደም አለይሂ ሰላም እና ማንኛውም ሰው የተፈጠረበት አላማ ነው ።

የሰው ልጆች የተፈጠሩበት አላማ አላህን በብቸኝነት ለመገዛት እንደሆነ አምላካችን አላህ ሱረቱል ዛሪያት ቁጥር 56 ላይ ይገልፅልናል አጋንትም ሰዎችም እንዲያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም ይላል ። ስለዚህ የመጀመሪያ ሰው አባታችን አደም አለይሂሰላም እስከሆነ ድረስ እሥልምና ሃይማኖት የሚጀምረው ከአባታችን አደም እንደሆነ ተረድቻለው ። ከአባታችን አደም ጀምሮ እስከ መጨረሻዉ ነቢይ ሙሐመድ ﷺ ድረስ የነበሩት ነቢያቶች ሁሉ እምነታቸው ኢሥላም እንደነበረና ጥሪያቸው ወደ እሥልምና እንደሆነ ተረድቻለው ።

የምሰራባቸው ሰዎች ሙሥሊሞች ናቸው ሁሌም ጠዋትና ማታ አያተል ቁርሲይን ይቀራሉ አይረሡትም ሁል ጊዜም ይቀሩታል ነገር ግን ለእኔ ተፅዕኖ አሳድሮብኝ ነበርና ትርጉሙን ማወቅ ፈለኩኝ አሳዩኝ እነርሱን ጠይቄያቸው ማለት ነው ።

ሱረቱል ኢኽላስ ላይ አላህ 1 እንደሆነ እና የሁሉም ነገር መጠጊያ እንደሆነ አልወለደም አልተወለደም ለእርሱም አምሳያ የለውም ነው የሚለው አያተል ኩርሲይ ላይ ስንመጣ ደግሞ ማብራሪያ ነው የሚሰጠን አምልኮ የሚገባው ለአላህ ብቻ እንደሆነ ከአላህ ዉጪ ሌላ አምላክ እንደሌለ ህያውና ራሱን ቻይ እንደሆነ ስለሚያብራራ ማንገላጀትም ሆነ እንቅልፍ አይዘውም ይላል አምላካችን አላህ ሱብሃነወታአላ ማንገላጀትም ሆነ እንቅልፍ አይዘውም ።

ወደ ክርስትና እምነት መመሪያ ስንመጣ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 4:38 ላይ እርሱም በስተኋላ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር አንቅተዉም መምህር ሆይ ስንሰምጥ አይገድህምንዴ አሉት ይለናል አምላካችን የሚሉት ኢየሱስ ክርስቶስ ተኝቶ ነበር ማለት ነው ። አምላካችን አላህ ሱብሃነህወታአላ ግን ማንገላጀትም ሆነ እንቅልፍ አይዘውም ። ስለዚ ማመን የነበረብን ማንገላጀትም ሆነ እንቅልፍ የማይዘውን አንድና ብቸኛ ፈጣሪ የሆነውን አላህን ብቻ ስለሆነ ወደ እሥልምና ሃይሜኖት ገብቻለው ።

እሥልምና የተቀበልኩኝ ለት በጣም ነው ደስ ያለኝ ከምናገረው በላይ የተፈጠርኩበትን አላማ አዉቄ ተቀብየ ተግባር ላይ ለማዋል ሀ ብየ የጀመርኩበት ቀን እስከ መቼም ድረስ ሁሌም የማረሳው ቀን ነው ቀኑ ጁምአ ቀን ነበር እንዳጋጣሚ ሆኖ ደግሞ አማኞች ለማየት የሚመኙትን መከተል ሙከረማ በአካል ተገኝቼ ያየሁበት ቀን ስለነበረ ሁሌም የማይረሳ ልዩ ቀን ነው ለእኔ።

ከእሥልምና ጸጋዎች እኔን ይበልጥ የማረከኝና የሳበኝ አንድ አምላክነቱ ሁለተኛ ሶስተኛ የሌለው አንድና ብቸኛ የሆነውን አምላካችን አላህ መገዛት ነው ። በመቀጠል እሥልምና ሚዛናዊና ፍትሀዊ የሆነ እምነት ነው።

ሂወት በእሥልምና አልሃምዱሊላህ በጣም ነዉ ደስ የሚለው እሥልምና የሚያዘው ለተፈጠርንበት አላማ እንድንንኖር ነው እናም ይሄ ትልቅ ኒዕማ ነው ። አልሃምዱሊለህ ። የበፊቱ ሂወቴና አሁን ያለሁበት ሂወቴ በጣም ልዩነት አለው ከጨለማ ወጥቼ ወደ ብርሃን እንደመጣው ያክል ተሰምቶኛል። ፈጣሪያችን አላህ ሁሉን ነገር ሲፈጥር የራሱ የሆነ ምክንያት አለው እኛን የሰው ልጆችን ደግሞ ሲፈጥር በብቼኝነት እንድንገዛ ነው ።
እና አሁን እኔ ባለሁበት ሂወቴ በጣም ደስተኛ ነኝ አልሃምዱሊላህ ።

በመጨረሻም ለማስተላለፍ የምፈልገዉ መልዕክት ከእሥልምና እምነት ዉጪ ያሉ የክርስትና እምነትም ሆነ የሌላ እምነት ተከታዮች ሁሉም የራሳቸው የሆነ መመሪያ አላቸዉ መመሪያችንን በደምብ ካነበብነዉና ፅንሰ ሀሳቡን ከተረዳነዉ እምነታችን መመሪያ መለኮታዊ ነዉ ወይስ ተሳሰቻለዉ የሚለዉን መለየት እንችላለን ከዚያ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራናል። በመቀጠል ደግሞ እምነታችንን ሰዎች እንዲመርጡልን መፍቀድ የለብንም እምነታችን የተፈጠርንበት አላማ አስከሆነ ድረስ መምረጥ ያለብን እኛዉ ነን ብናምን የምንጠቀም እኛው ነን ብንክድም የምንጎዳው እኛው ነን።

እና ደግሞ አንዳዶቹ እሥልምና እምነት ትክክለኛ እምነት መሆኑን ያውቃሉ ግን ደፍረው ለመግባት ፈርተው ዳር ላይ ቆመው የሚመለከቱ አሉ እነዚያ ያስፈራቸው ነገር ቤተሰብ ወይም ዘመድ ይርቀናል በሚል ነው ። ቤተሰብ ሆነ ወዳጅ ዘመድ ሊርቁን ይችላሉ ግን ለእነርሱ መልካም እንድንሆን አላህም ያዘናል መልካምነታችን ግን ገደብ አለው ።

ለምሳሌ ሱረቱል አንከተቡት ቀጥር 8 ላይ ሰውንም ለወላጆቹ መልካም እንዲሆን አዘዝን ግን በርሱ እውቀት የሌለው አንዳች ነገር በእኔ ላይ እንድታጋራ ቢያዙህ ፈጽሞ አትታዘዛቸው ሁላቸውንም መመለሻቹ ወደ እኔ ነው ትሰሩት የነበረውን ሁሉ እነግራችኃለው ይለናል ስለዚህ ለቤተሰቦቻችን መልካም መሆን እንዳለ ሆኖ ግን በአላህ ማጋራት የለብንም ወደ እሥልምና መግባታቹ የምታጡት ነገር የለም ወደ እሥልምና ግቡ ነው የምለው አመሰግናለው ።
ትርንጎ




ጥያቄ ስጠይቃቸው ጥያቄ አትጠይቂን ይሉኝ ነበር የሃይማኖት አባቶች ። ሠለምቴዋ ትእግስት በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም በቁጥር 32





የሠለምቴዎችን ልዩ የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኳቸውን ለማድመጥ :-





AS_HABULE YAMlNE TUBE
https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q

በጹሑፍ ይቀርባል ¶
https://t.me/AshaBuleyamine/5125