Get Mystery Box with random crypto!

ቢስሚላህ ወደ እስልምና የመጣው ወንድማችሁ ነኝ ። ታሪኬ ይጠቅማል ብዬ ስላሰብኩኝ ነው በእንዴት | AS-HABULE YEMINE (የቀኝ ጓዶች) ማህደር

ቢስሚላህ
ወደ እስልምና የመጣው ወንድማችሁ ነኝ ። ታሪኬ ይጠቅማል ብዬ ስላሰብኩኝ ነው በእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ላካፍላችሁ የፈለኩት ።

እስልምና መርጦኛል አልሃምዱሊላህ

ስሜ አብዲሳ እምሩ ይባላል የምኖረው በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጭሮ(አሰበ ተፈሪ) ሲሆን በአሏህ እዝነት ታሪኬን ላካፍላችሁ ወደጃለው አሏህ በራህመቱ በ2010 የኦርቶዶክስ ፆም ውስጥ ነበር የሰለምኩት(ከክህደት አለም የወጣሁት) ነገሩ ወዲህ ነው ስምንተኛ ክፍል እስክደርስ ድረስ የኖርኩት ካፊሮች (ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች) የሚበዙበት ሰፈር ነው ግን ልክ 2008 አካባቢ ስምንተኛ ክፍል ሳለው ሙስሊሞች ሚበዙበት ሰፈር 90% የሚሆኑት የሰፈሩ ነዋሪዎች ሙስሊም የሆኑ ሰፈር ገባን ሁለት አመት እዛ ከኖርን በኃላ ከሰፈሩ ሰው እየተላመድን ስንመጣ እኔም ከሙስሊም ልጆች ጋር ጓደኝነት ጀመርኩ ይሄን ጊዜ ነው እንግዲ የሂዳያ ስጦታዬን ለማግኘት ጉዞ የጀመርኩት።

ለጥናት ከሙስሊም ልጆች ጋር በምንገናኝበት ጊዜ ስለእምነት Discuss እናደርግ ነበር ።አንዳንዴም የከፋ ሙግት አደርግ ነበር! ከሙስሊም ጓደኞቼ ሀዲሶችን እሰማ ነበር ብዙ ጊዜ የእየሱስ ክርስቶስ (ነቢ ኢሳ) አሌይሂ ሰላም አልሞተም አልተሰቀለም የምትለዋን ነገር ስሰማ በጣም እናደድ ነበር። አንዳንድ ቀን ለብቻዬን ቁጭ ብዬ ልስለም አልስለም ብዬ ከአእምሮዬ ጋር ግጥሚያ ጀመርኩ

........."አሁን ልስለም ብል ቤተሰቦቼን ትቼ ነው ምሰልመው አይ ይቅርብኝ እነሱን ትቼ ከምሰልም ይቅርብኝ አይ" ብዬ ከአእምሮዬ ጋር ከባድ ጦርነት ገጥም ነበር ግን ከእለታት አንድ ቀን የህይወቴ turning point (ህይወቴ የተለወጠበት) ቀን ላይ ደረስኩ ትዝ ይለኛልእኔ እና ሁለት የሙስሊም ጓደኞቼ ቁጭ ብለን ባለንበት ምላሴ ከአእምሮዬ ጋር ሳይማከር በድንገት ሙስሊም መሆን ፈልጋለው የሚል ቃል ተናገረ!

ከዛ እነሱም የሰሙትን ማመን አቅቷቸው እ እ እያሉ በግርምት ያዩኝ ጀመር እኔም በድጋሚ አው ሙስሊም ለመሆን ምን ማድረግ አለብኝ ብዬ ጠየኳቸው እነሱም ምንም ማድረግ አይጠበቅብህም ሸሀዳ ብቻ ማለት ነው ሚያስፈልግህ ። ከአንገቴ ላይ ካንጠለጠልኩት
የሽርክ ገመድ እና መስቀል በሸሀዳ ቃል ድኛለው (መሬት ላይ ያለ ነገር በሙሉ የሷን ያህል መመዘን የማይችለውን ቃል) አልኩኝ በአሏህ እዝነት አልሀምዱሊላህ ወደ ተወለድኩበት እምነት ወደ እስልምና ተመለስኩ ወርቃማ ብዬ መግለፅ ማልችለው ስጦታ ከአሏህ ተበረከተልኝ.............

. ኢንሻ አሏህ ክፍል ሁለት ይቀጥላል አብዲሳ ነኝ ሠለምቴው ። ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ

የሠለምቴዎችን ታሪክ ለመከታተል ይወዳጁን
የሠለምቴዎችን ልዩ የእንዴት ሰለምኩኝ ፕሮግራም ታሪኳቸውን ለማድመጥ :-





AS_HABULE YAMlNE TUBE

https://youtube.com/channel/UCGL4i2pl7eV7sWA3yvsno_Q

በጹሑፍ ይቀርባል ¶
https://t.me/AshaBuleyamine/5125

ሠለምቴ ከሆኑ ጆይን ብለው የፕሮግራሙ እንግዳ ይሁኑ
https://t.me/Selmeta

አስተያየት ለመስጠት
http://t.me//Ashabulyeminbot

ለበለጠ መረጃ
https://t.me/Quran_is_life_Sari_A