Get Mystery Box with random crypto!

'ሀ' ብለህ ከትምህርት 'ዋ' ብለህ ከህይወት ትማራለህ። ሁሉም ተማሪ የሆነበት ቦታ ቢኖር ህይ | መፅሐፍት

"ሀ" ብለህ ከትምህርት "ዋ" ብለህ ከህይወት ትማራለህ።

ሁሉም ተማሪ የሆነበት ቦታ ቢኖር ህይወት ይባላል። ትልቁ፣ ትንሹም፣ ረጅሙም፣ አጭሩ፣ የገባው፣ የላገባው፣ ሀብታም፣ ድሀው፣ የተማረው፣ የልተማረው በአጠቃላይ ሁሉም ተማረ ነው የህይወት። ለብዙዎች ተማረ ማለት የትምህርት ቤት ክፍል ውስጥ የሚገኝ፤ ደብተርና እስክሪቢቶ ያለው፣ ቦርሳ ይዞ የሚመጠ ይመስላቸዋል ግን ተማሪ ከዚያ ያለፈ ነው። ተማሪ ማለት ማወቅ ያለበት ነገር ለማወቅ የሚተጋ፣ ጆሮ በደንብ የሚጠቀምና መናገር ባለበት ሰዓት የሚናገር ነው። የፈለከው ያህል ጉበዝ ተማሪ ብትሆንም ስህትት መስራትህ ግን አይቀርም እናም ከስህተት ተማር እንጂ ስህተቱ አንተ እንደሆንክ አታስብ። አንዳንዴ የወደቅበት ቦታ አትጥላ ምክንያቱም ስህተትህን አሳይቶሀልና።

ለመስማት የቸኮለና ለመናገር የዘገየ መሆንን የመሰለ ነገር የለም። አስተዋይ የሚናገረው ነገር የሚያውቅና የሚሰመው ነገር በሙሉ የማይቀበልና የማያጥላላ ነው። ስትወድቅ ተነስ፤ ከውድቀት ተማር እንጂ የወደቅበት ቦታ ላይ የህልምህ መቃብር አታድርግ።ህይወት ሰበረች አትበል፤ ህይወት ሳይሆን የሰበረህ የተሰበርክበት ቁስል ስታክ ነው የባሰ የተሰበርከው። እናም ህይወት ከፍታ አለው እንደዛውም ዝቅታ አለው፤ ማግኛት አለው እንደዛውም ማጣት አለው፤ እናም ይህ ሁሉ የህይወት አካል ናቸው። ስለዚህ ሲጨልም እንደሚናገም ባምን አሁን የለው ጨለም ግን እንዴት አድርጌ መገፈጥ እንደለብኝ ማውቅ አለብኝ። እናም ሁሌም ተማሪ ሁን፤ ከመናገር ይልቅ መስማት አስቀድም።

@BarkoteA