Get Mystery Box with random crypto!

#ችግርማ_አለ ....... #መቼ? እሳት ተለኩሶ ጥሬው ካልበሰለ በጠዋት ተለፍቶ ኑሮ ካልቀለለ | መፅሐፍት

#ችግርማ_አለ ....... #መቼ?

እሳት ተለኩሶ ጥሬው ካልበሰለ
በጠዋት ተለፍቶ ኑሮ ካልቀለለ

ችግር አለ.....

ስልጠና ተሰቶ ለውጥ ካልበቀለ
አረም መንቀል ትቶ ዘርን ከነቀለ

ችግር አለ.....

ሙሉ ቀን ተምሮ እውቀት ካልገበየ
ለሕይወት ጥያቄ መልሱን ካዘገየ

ችግር አለ....

መሰረት ሳይጣል ቤት ከተዋቀረ
ማንነት ተዛብቶ ነብስ ከጨፈረ

ችግር አለ.....

ወልድ በሌለበት ፅድቅ ከታወጀ
ሰው ራሱን ለማዳን አመታት ከፈጀ

ችግር አለ.....

ሰው በራሱ ፅድቅ ፀጋን ከሸፈነ
አምላክ ጋ ለመድረስ በሕግ ከመነነ

ችግር አለ.....

@BarkoteA