Get Mystery Box with random crypto!

በፍቅር ሱባኤ በረሀብ በረሀ በስጋ ጠውልገን በፍቅር ሰማይ ስር ከሚያፈሰው ዝናብ በመንፈስ አብበ | መፅሐፍት

በፍቅር ሱባኤ
በረሀብ በረሀ በስጋ ጠውልገን
በፍቅር ሰማይ ስር ከሚያፈሰው ዝናብ በመንፈስ አብበን
ከንፈራችን ደርቆ አየተዛዘንን
አናርሰው ነበር እየተቃመስን
እስትንፋስ ሳይቀረን እየተዋዋስን

ከቤታችን ጀርባ ባለች ትንሽ ደብር እቤት
አንዳችን ላንዳችን ስንፀልይ ውለን
ባገኘናት ጉርሻ አፋችን አብሰን
በፍቅር ሱባኤ ደስተኞች ነበርን

ትዝ ይልሻል ወዴ?
ክረምትና በጋን
የአልጋችንን ቦታ ሳንቀይር ረስተን
ሁሌ በጋ መስሎን
ዝናብ የጣለ ቀን
አልጋችን እርሶ እረጥቦ ገላችን
ተቃቅፈን ያደርነው እያንቀጠቀጠን
ለሌላ ያየ ሰው የችግር ቢመስልም
ለኛ ፍቅር ነበር

ደግሞ ለበዓል ቀን ፊታችን ሲያበራ
ለስላሳ እንጀራ በወጥ ተፈትፍታ ቤታችን ስትገባ
ሙቀቱ ሲያጅበን የጠጅ እና የጠላ
ሰው ሆንን እያልን
አቅም በአንድ ቀን እንደተላበስን
ስንጮት ያደርነው ቀኑ እስኪነጋ እንቅልፍ ሳየጥለን
የዛች ቀኗን ማግስት ከአልጋችን ወለን
ላንነሳ ምለን

ያሳለፍነው ሁሉ እውነት ትዝ ይልሻል
አውቃለሁኝ ውዴ አዎን አስታውሰሻል
ከቤታችን መሀል የጣልሽው ትዝታሽ አግኝቶ ነግሮሻል
ድሮስ ያለ ፍቅር አሁን ያለሽ ሁሉ መቼ ይጠቅምሻል
ልብሽ ከኔ ኋሏ ብዙ ጠይቆሻል

ያኔ ግን
ከኔ ጋራ ሳለሽ ደሀ እንኳ ብኖንም
ቤታችንን በግንብ ባናንፅ ባናሽቆጠቁጥም
ሆዳችን ለሁሌ ጠግቦልን ባያድርም
የኔና ያንቺ ህይወት አንድ ቀን ተሳስቶ አማሮን አያውቅም

@MyMessagesss