Get Mystery Box with random crypto!

ጠቢብ ማነው ላሉ                            አእላፍ ቃል ቢወጡ ፤ ዜማ ቢደረደር | መፅሐፍት

ጠቢብ ማነው ላሉ
                          
አእላፍ ቃል ቢወጡ ፤ ዜማ ቢደረደር
የሰው ልጅ ሃሳቡ ፤ ተዝቆ ቢከመር
ትዝታ ቢወሳ ፤ ጊዜ ላይመለስ
በፍቅር ቢጎዳ
የፈሰሰ ፍቅር ፤ ዳግም ላይታፈስ

ፍጥረቱ ይገርማል
ከቶ ተስፋ አይቆርጥም ፤ አሁንም ይፅፋል
ከመዳፉ መሃል
ከጣቶቹ ጫፎች ፤ ውብ ምስል ይፈልቃል

ሰው ሰውን ያስባለው ፤ ለካ ተስፋ ነበር
ስባሪ ልብ ይዞ ፤ ትዝታ ላይ መሰፍር
ህያው ነኝ እያለ ፤ ተስፋ ይዞ መቀበር
ታድያ
ይህን መሰል ስሜት ፤ ቃላት ቢደረደር
ከንፁህ ሸራ ላይ ፤ ውብ ቀለም ቢሰፍር
እውነት ስሜት ጥሎ ፤ ምን አለ የሚናገር
 
ንፁህ ሰው ካገኙ ፤ ፍፁም ሚዘርፋቸው
ህመምም ስዕል ነው ፤ እንባም ቅኔ ናቸው
ጣት ቀለም ቢያሳምር ፤ አንደበት ቃል ቢቃኝ
ከቶ አንድም ጠቢብ
እነደ ህመም አይስልም ፤ እንደ እንባ አይቃኝ

@MyMessagesss