Get Mystery Box with random crypto!

ወደው አይስቁ በሃዘን ዶፍ ዥረት ማህበል ሲናጡ ኑሮ ሁሉ ሲሆን ከድጥ ወደማጡ አይን ደርቆ ሲቀ | መፅሐፍት

ወደው አይስቁ

በሃዘን ዶፍ ዥረት
ማህበል ሲናጡ
ኑሮ ሁሉ ሲሆን
ከድጥ ወደማጡ
አይን ደርቆ ሲቀር
ማንባት እያቃጣው
አንደበት ዝም ሲል
ማውራት እያሰኘው
በውሸት አሉ ባልታ
ሲደነቁር ጆሮ
መኖር እየሻቱ
እጅግ ሲመር ኑሮ
ያገለሉት ቀርቶ
ያቀረቡት ሲሸሽ
ነገር ሁሉ ሲሆን
የተገላቢጦሽ
በነገሮች ግርምት
ካልተነቀነቁ
በዋዛ ፈዛዛ
ለካስ ወደው አይስቁ

https://t.me/MyMessagesss