Get Mystery Box with random crypto!

'እኔ አንተን ሳጠና' ...........እኔ አንተን ሳጠና ሒሳብ አስተማሪ Xን ለመፈለግ እን | መፅሐፍት

"እኔ አንተን ሳጠና"

...........እኔ አንተን ሳጠና
ሒሳብ አስተማሪ
Xን ለመፈለግ
እንደወጣ ቀረ
ሆነና መርማሪ
በጠመኔ ብርታት
በጀመረው ጉዞ
አማርኛ መምህር
ድንገት አገኘሁት
ከትምህርት ተወግዞ
ምዕራፍ አንድ ብሎ
ሳይንስ ለማስተማር
ሲቀጥል መምህሬ
ምዕራፍ ዘጠኝ ገባ
እኔ አንተን ሳጠና
ቆሜ ተገትሬ፡፡
..........ከደጀ ሰላሙ
ከቤተ መቅደሱ
ቆሜ ለመቀደስ
ያስለቅቀኝ ብዬ
ምን አልባት እጣኑ
"እትሁ በሰላም"
ብሎ ገላገለው
"አሀዱ አብ"
ብለው የተጀመረውን
የቄሱን ምስገና ጨርሶ ዲያቆኑ፡፡
................ ይኸውልህ ውዴ
እኔ አንተን ሳጠና
ከመንበሩ ወርዶ
ንጉስ ደጅ ጠና
የሰማዩ ፀሃይ
አፍቅሮ ጨረቃን
እሷኑ ሲከተል
እኛን እረሳና
ይኸው ብርሃን ነሳን፡፡
.............ይኸውል ፍቅሬ
እኔ አንተን ሳጠና
ጥቁረቱን ለቀቀ
ጠጉሬም ነጣና
ምርኩዝ ተደገፈ
እግሬም ዛለና
ብህሬም ደርቆ ቀረ
ቀለሜ አለቀና
እንደ ጨው ሞሞልህ
አይኔም ፈዘዘና
ድድ ብቻ ሆነ
ያምራል ምትለኝ
ጥርሴም ወለቀና፡፡
.........አድምጠኝ የኔ አለም
ካንተ እደርስ ብዬ
የሆንኩትን ሁላ
እንዲሁ ቀረውልህ
ከሜዳ ወድቄ
ሆኜልህ ተላላ
አጠናለው ብዬ
ስላንተ አፈጣጠር
ደብተሬን ብገልፀው
አጣው አንተነትክን
አይደለም ከጥራዝ
አለም ላይ ባስሰው፡፡
...........ካገኘውህ ብዬ
ከዚች ጠባብ ምድር
እኔ አንተን ሳጠና
አገኘውሁ ድንገት
ከአለም ከሚሰፋ
ከልቤ ደጃፍ ስር
ብርሃነኔ ሆንክና፡፡


https://t.me/MyMessagesss