🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

​​የመፅሐፍ አጭር ዳሰሳ ለውጥ የመፅሐፉ ጭብጥ የለውጥ ሁሉ መሠረቱ የአስተሳሰብ ለውጥ ነው ብ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

​​የመፅሐፍ አጭር ዳሰሳ

ለውጥ

የመፅሐፉ ጭብጥ የለውጥ ሁሉ መሠረቱ የአስተሳሰብ ለውጥ ነው ብሎ እንደሚያስቀምጥ እገምታለሁ። ለዚያም ትኩረት አድርጎ መሠረታዊ የለውጥ ምሶሶዎችን በተለየ አቀራረብ ይተርካል።
እኛ ሰዎች ለመለወጥ ስናስብ እና እርምጃ ስንጀምርም ከምንም በፊት ነባር አሉታዊና ጎታች አስተሳሰቦችን በመተው በተቃና አስተሳሰብ መቃኘት እንዳለብን አመክሮ ይተነትናል።

በመፅሃፉ በምናብ ስለምናስባቸው አንድ ልሂቅ ስብዕና ይተርካል። የግለሰቡ ስብዕና ጣዕም ምስጢሮቹም በየምዕራፉ ተወስተዋል። ሕይወትን እንዴት እንደረዱት? ፣ የእስልምና እና ንባብን ወዳጅነት ፣ ተደራሲያንስ እንዴት ከእዚህ ግሩም ስብዕና ጋር መቆራኘት እንደሚችሉ ይተርካል።

መፅሐፉ ሲጀምር ትልቁን መሠረት የሚጥለው በኡስታዝ ሉቅማን ስብዕና ላይ ነው። እንዲሁም ከእርሳቸው ጋር ስላሉት ተማሪዎቻቸው እና ስለወሰዱት መሠረታዊ የህይወት መርሆዎች ያስቀምጣል።

ስለ ዕውቀት ፣ስለ አእምሮ አቅም ፣ ስለ ፍቅርና ተስፋ በኡስታዝ ሉቅማን መካሪነት ይቀሰማል።ሉቅማን ከመሠረቱም በእድሜ የገዘፉ በእውቀት የደረጁ በመሆናቸው ከእርሳቸው ብዙ እውቀቶችን ያገኛሉ።

እንዲሁም ስለቤተመፅሐፍት ፣ ንባብና ጥቅም ፣ የተለያዩ የንባብ ፕሮጀክቶችን በሚተገበር እና በተለየ መንገድ ያቀርባል። አክሎም በማሕበረሰቡ ውስጥ ለውጥ እንዴት እንደሚመጣ ብዙ ሐሳቦችን ይጠቁማል።

መፅሐፉ በልብወለድ መልኩ ቢቀርብም በገሃዱ ዓለም ለመሳል ጥረት እንድናደርግ የሚለፋ በርካታ እውነታዎችን ስሎ ያስቀምጣል።

ከመፅሐፉ ገፆች ውስጥ...

«የአካልን ምቾት ሊያስጠብቅ የሚማስነው የዘመናችን ስልጣኔ በመንፈሳዊነት ረሃብ ወድቆ መማቀቁ እሙን ነው ። በመጨረሻም ሊያረካው የሚለፋለትን አካሉን ከምድረ-ገፅ ሲያጠፋ ይስተዋላል። ከመንፈሳዊነት የተራቆተ ቁሳዊ ስልጣኔ ብቻውን ለሰው ልጅ ተስማሚ አይደለምና»
▯ለውጥ ▯

▯▯ኡስታዝ ኢንጂነር በድሩ ሁሴን ▯▯

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19