🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

​​የሚከተለው ግጥም ከታች በሚታየው ታሪካዊ ፎቶግራፍ ንሸጣ የተፃፈ ነው፤በፎቶው ላይ ሻምበል አበበ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

​​የሚከተለው ግጥም ከታች በሚታየው ታሪካዊ ፎቶግራፍ ንሸጣ የተፃፈ ነው፤በፎቶው ላይ ሻምበል አበበ ቢቂላ የልምምድ ሩጫ ሲሮጥ ይታያል፤ ከሁዋላው አህያ እየነዳ የሚያልፍ አላፊ ጠፊ ገበሬ አለ፤ ግጥሙን የጣፍኩት ለዚህ አህያ ነጂ ገበሬ ነው፤ )
ላንድ ላልታወቀ አህያ ነጂ
(በእውቀቱ ስዩም)
ባሮጌው ጎዳና፤ በጮርቃው ማለዳ
ጋልቦ እንዳልደከመ፤ እንደ ጥቁር ፈርዳ
አቤ እየሠገረ
ከኋላው የሚሳብ፤ አህያ እየነዳ
ስሙ ማን ነበረ?
የመንደር ወፍጮ ቤት፤ ቅሪቱን ሲተፋ
ዱቄት የሚለብሰው
በዝነኞች ፊት ላይ፤ ካሜራ ሲያካፋ
ጠብታ ሚደርሰው
ማን ይሆን ይሄ ሰው?
እኛ የምናዘው፤ እሱ የሚሰማን
ሰው እያደረገን፤ ከሰው የማንቆጥረው
አህያ እየነዳ፤ አስፋልቱን ሲሻማን
የምንገፈትረው፤
በጥሩምባ እሩምታ፤ ምናስደነብረው፤
በኑሮው ምንቀልድ፤ በሞቱ ምንተርት
በፈረሰ ጎጆው፤ ፓርቲ ምንመሠርት፤
ፊቱ ቢልቦርድ ላይ፤ ወጥቶ ባይሰጣ
ጀግና የማይባል
ግና ለጀግኖቹ፤ ጉልበት የሚያዋጣ፡፡
ካበበ ሰሀን ላይ፤ በሶው እንዳይጠፋ
በተራ ክንዶቹ፤ ተራራ ሚገፋ
ለናቀችው ዓለም፤ ላቡን የገበረ
ስሙ ማን ነበረ?

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19