🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ጥያቄ? ልብ ስጋ ነው ወይ ነፍስ ?? ____ ተይ በታቦቱ ተይ በሰማእቱ ተይ በአርባራቱ ላስይዝ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ጥያቄ?
ልብ ስጋ ነው ወይ ነፍስ ??
____
ተይ በታቦቱ
ተይ በሰማእቱ
ተይ በአርባራቱ

ላስይዝሽ እባክሽ በእናትዋ ባታ
በተወለድሽባት በቅብአ ቦታ

ታቦት ብዘረዝር ጎንደሬ አረጉኝ
አድባር ብጠራ ጎጃሜ ነህ አሉኝ

ይቆጠራል እንዴ ታቦት በአንድ አድባር
እምነት ለዓለም ነው ማን ሰጠው ለአባናር

ጥያቄ ?

ታቦትን ለጎንደር የሰጠውስ ማነው
አባይን ለጎጃም የሰጠውስ ማነው
የኔን ልብ ላንቺ የሰጠውስ ማነው
እንደው አትፍረጂ ያው ያንቺ አምላክ ነው
ወንድ አዳም ልቤን፥ በሔዋን ሚያመልከው
ያፈቀረ ንፉግ እግዜር ከየት ሊያቀው?

መልስ ?

ታቦቱን ማንሳቴ
ጠበሉን ማንሳቴ
እንድትመጭ ነበር ያስያዝኩሽ በእምነቴ

እምነቴ አልበጀኝ ለልቤ ባረዳ
ነፍስ አፀድቅ ተብሎ ስጋ ለሚጎዳ

ምንድነው መልሱ?
ጥያቄ?

ልብ ግን ስጋ ነው?
ከስጋ ተርታ ነውስ ሚመደበው?
ወይስ
ከነፍስስ ነው?
በእግዜር ዘንድ በሰማይ ሚታዬው ?

እና
የስጋ ከሆነስ ለፅድቅ ይሆናል?
አንቺን ማፍቀሬ ለነፍስስ ይባላል?

መልሽልኝ ????

ግዕዝ ሙላት

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19