🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የትም ፍጭው……… የኔ ልጅ ጨዋ ነው፤ ውሎው ከስራ ነው። የምፈልገውን የሰኘኝን ሁላ፣ እንዳይጎል | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የትም ፍጭው………

የኔ ልጅ ጨዋ ነው፤
ውሎው ከስራ ነው።
የምፈልገውን የሰኘኝን ሁላ፣
እንዳይጎል ያደርጋል ሁሉን እያሟላ።
ልጄ እኮ ልባም ነው፤
ጥሩ ደሞዝ ያለው፤
ብር እንካ የሚለኝ፤
ጠጅ የሚገዛልኝ፤
ሁሉን የሚሰጠኝ፤
ስራውምንእንደሆን
ጠንቅቄየማላውቀው፣
ልጄ እኮ ሌባ ነው።

≈ ተፃፈ በኤሮስ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19