🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

----እውነት፣ተስፋና ፍቅር---- በሐዘን ቤት እንባ ይነዳል፤ እቶን ሆኖ በቀዬ ላይ ይቃጠላል፤ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

----እውነት፣ተስፋና ፍቅር----

በሐዘን ቤት እንባ ይነዳል፤
እቶን ሆኖ በቀዬ ላይ ይቃጠላል፤
የወላፈን ጅራፍ፥ስቦ ይገርፈኛል።
ግማሽ ልቤን በእቅፉ ውስጥ እያሞቀ፤
የቀረውን በጅራፉ ሞሸለቀ።
.......
ዝቅ ስል ሲዖል ላይ አፈጠጥኩ፤
ከዛም ዘወር ስል፥ከሞት ጋር ተፋጠጥኩ፤
ዙሪያ ገባ ሞት ነው፤መላክ መሳይ ሰይጣን፤
እኔና ሰላሜን እንቅልፍ የሚነሳን።
.......
ተስፋ ርቆ ሸሽቶ ሄደ፤
ፍቅር ዋጋው ከርሞ ናኘ፤
ልቤ ቅስሙ ተሰባብሮ.....ሊደንዝ ዘንድ 'እየተመኘ።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ማየት ተውኩኝ፥ጸሐይ ሄዳ፥ብርሃን ጠፍቶ፤
በጠፈር ሀይል፥ጽልመት ባህር፥ውብ ፀዳሏ ተሰውቶ ፤
አይሄድ ይመስል የሚያበራው፥ያ ውበቷ፣
ከዋክብትን የሚሸፍን፥ደም ግባቷ፣
አለሁ ብሎ የደለለኝ፣
በፍቅር ቀትር፥በደስታው ጨጅ ያሰከረኝ፣
ጀንበር ገብታ፥ጥላኝ ስትሄድ ተነጠለኝ።
...
እኔ ምስኪን መፃተኛ፣
በፀሀይ ናፍቆት የምቃትት፥የማልተኛ፣
ነግቶ አያት ዘንድ ጠብቃለሁ፤
ብርሃነ ፍቀሬ ሆይ......
እስክትመጪ ድረስ......ኩራዜን ይዣለሁ።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

በልቤ ግድግዳ ትልልልልልቅ ስዕል አለ፤
ውበትን የሚያስንቅ፥መልክሽን ያዘለ፤
እሱ ብቻ እንዲታይ፥
እሱ ብቻ እንዲደምቅ፥ሁሉን የከለለ፤
......
በልቤ ግድግዳ......
እንቡጥ ከንፈሮችሽ፣
አበባ ጉንጮችሽ፥
ደሜን ይጣራሉ፣
"ና ሳመን...ና ሳመን....ና ሳመን" እያሉ።
........
በአይኖችሽ ነጸብራቅ ምሉዕ ፊትሽ በርቷል፤
ልክ እንደ ፈንዲሻ፥ፈገግታሽ ፈንድቷል፤
ያ መረዋ ድምጽሽ፣
ያ መረዋ ድምጽሽ፣
እንኳን ከንቱ ልቤን፥መለዐክትን ይጣራል።
.........
እቴ ባንቺ ፍቅር ልቤ እየነደደ፣
እግርሽ በረገጠው፥ጎዳና እየሔደ፤
ባይኖችሽ ጮራ ስር እንደ ጨው አምድ ሲናድ፣
በፈገግታሽ ሞገድ፥ወኔ እብሪቴ ሲርድ፣
ፍቅር ያሳሳው ልቤ....
ፍቅር ያሳሳው ልቤ...
መከተል አድክሞት፥'እንደ ንፋስ ነፈሰ፤
ጨዋታ ፈረሰ፥ዳቦውም ተቆረሰ።

~ተፃፈ በኢሮስ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19