Get Mystery Box with random crypto!

አምላክ ይክፈልልኝ አንቺ እማምዬ ...እስቲ ልጠይቅሽ ስንት ነው መጠኑ ስንት ያወጣል ፍቅርሽ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አምላክ ይክፈልልኝ
አንቺ እማምዬ ...እስቲ ልጠይቅሽ
ስንት ነው መጠኑ ስንት ያወጣል ፍቅርሽ
ማሰብ አቅቶኛል እንኳንስ ልክስሽ
እንኳንስ ልክስሽ አቅቶኛል ማሰብ
በስንት ይታመናል ልጆችን መሰብሰብ
በምን ይከፈላል ከራስ ቆርሶ ማጉረስ
ስንት ያወጣልና ለልጅ ህመም ማልቀስ
ንገሪኝ ልክፈለው ስንት ነው ሚበቃሽ
እድሜሽ ስንት ያወጣል ለኔ ስትይ ኖረሽ
ልከፍልሽ ባልችልም ያዢ ልመርቅሽ
የዘላለም ጌታ አንቺን ያኑርልኝ
መሶብሽ ሙሉ ይሁን ጎሎሽ አያሳየኝ
በረከትሽ ይብዛ
ሳቅሽ ድርብ ይሁን አንቺን አይክፋብኝ
እኔ ምን አቅም አለኝ አምላክ ይክፈልልኝ።


ከ ናቲ የሳራ ልጅ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19