2022-02-19 10:23:54
#Update
' ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ' ትላንት በራሱ ቡድን የተተከለውን የመጀመሪያ የኔትዎርክ ጣቢያ በተሳካ ሁኔታ አጠናቆ ለሥራ ዝግጁ ማድረጉን አሳውቆናል።
የመጀመሪያው ጣቢያ የተተከለው በአዲስ አበባ ነው።
ድርጅቱ ፥ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ ለመግባት ፍቃድ ሲያገኝ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ኔትወርክ ለመገንባት ቃል ገብቶ እንደነበር አስታውሷል።
በራሱ ቡድን የተተከለው የመጀመሪያ ጣቢያ በተሳካ ሁኔታ አጠናቆ ለሥራ ዝግጁ መሆኑ የዚህ ማሳያ ነው ብሎታል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ይህን የመሰሉ ጣቢያዎች ደንበኞቹ ጋር ለመድረስ የሚያስችሉት የመጨረሻዎቹ ክፍሎች መሆናቸውን አስረድቷል።
የመጀመሪያው ጣቢያ በአዲስ አበባ የተተከለ ሲሆን በቀጣይ በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ይተከላሉ ብሏል።
ሳፋሪኮም አገልግሎቱን ለመጀመር በተዘጋጀበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ እውን የሚያደርግ ጥራት ያለው ኔትዎርክ የመገንባት ጥረቱን አፋጥኖ እንደሚቀጥል ገልጿል።
ይህ ወር የሚያኮሩ ወሳኝ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው ያለው ሳፋሪኮም ዋና መስሪያ ቤቱን የገባንበት፤ የተሳካ የመጀመሪያ ጥሪ ያደረገበት ፣ አሁን ደግሞ የራሱን የኔትዎርክ ጣቢያ የተከለበት መሆኑን አሳውቆናል።
በሂደቱ ለተመዘገበው ስኬት ያለእረፍት ሲሰሩ ለነበሩት ባልደረቦቹ እና አጋሮቹ እንዲሁም አስፈላጊውን ድጋፍ ለሚያሰርግለት የኢትዮጵያ መንግስት ምስጋና አቅርቧል።
#fidelpost
1.2K viewsBirhan Nega, edited 07:23