🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

DW Amharic

Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic D
Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic
Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 43.22K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 13

2023-05-03 20:21:35 የሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ዐርዕስተ ዜና

በኢትዮጵያ መንግሥትና ራሱን “የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት” ብሎ በሚጠራው ቡድን መካከል ዛንዚባር ታንዛኒያ ውስጥ ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያ ዙር የሰላም ውይይት ዛሬ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንግሥትና “የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት” አስታወቁ። ሆኖም የኢትዮጵያ መንግሥት እንዳለው በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ መስማማት አልቻሉም። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትም ቁልፍ በሆኑ የፖለቲካ ጉዳዮች ባላቸው ላይ መስማማት አለመቻላቸውን ገልጿል።

የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ቃል የገቡት የተኩስ አቁም እንዲጸና ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ዛሬም በተለያዩ የሱዳን ከተሞች ተኩስ ሲሰማ ነበር። ተፋላሚዎቹ ጀነራሎች ተኩስ ለማቆም የገቡትን ቃል አለመጠበቃቸው ዓለም አቀፍ ትችት አስከትሏል።

በሰሜንና ምዕራብ ሩዋንዳ ፣ ጎርፍ ከ120 በላይ ሰዎችን ገደለ ። የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት የፖል ካጋሜ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው በሰሜንና ምዕራብ ሩዋንዳ ትናንት ለሊት የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ቢያንስ 129 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። የሟቾቹ ቁጥር ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ሙሉውን ዜና ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ
https://p.dw.com/p/4QrHk?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
4.2K viewsDW Amharic, 17:21
Open / Comment
2023-05-03 20:17:57 https://p.dw.com/p/4QqSQ?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
3.8K viewsDW Amharic, 17:17
Open / Comment
2023-05-03 20:16:01 https://p.dw.com/p/4QrF9?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
3.3K viewsDW Amharic, 17:16
Open / Comment
2023-05-03 20:12:47 https://p.dw.com/p/4QrGW?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
3.0K viewsDW Amharic, 17:12
Open / Comment
2023-05-03 20:11:05 https://p.dw.com/p/4QqJb?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
3.0K viewsDW Amharic, 17:11
Open / Comment
2023-05-03 20:10:29 https://p.dw.com/p/4QrHY?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
3.0K viewsDW Amharic, 17:10
Open / Comment
2023-05-03 20:00:11 Live stream finished (1 hour)
17:00
Open / Comment
2023-05-03 18:19:39
በትግራይ ክልል የሰብአዊ አቅርቦት ካቆመ ከ20 ቀናት በላይ ተቆጠረ

የዓለም ምግብ ድርጅት ለትግራይ ክልል የሰብአዊ ርዳታ አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ካቆመ ከ20 ቀናት በላይ ማለፉን የክልሉ አስተዳደር ዐስታወቀ ። የክልሉ የአደጋ መከላከል ኮሚሽን፦ ለትግራይ ክልል ይላክ የነበረው ሰብአዊ ርዳታ መቋረጡን «አስደንጋጭ» ብሎታል ። ከ6 ሚልዮን በላይ የሚገመት በትግራይ ክልል ያለ ርዳታ ፈላጊ ሕይወትንም አደጋ ላይ የሚጥል ሲል ገልጿታል ።

ትናንት ከዓለም የምግብ ድርጅት በኩል የተሰማው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ተቋሙ ለትግራይ ክልል የሚሰጠውን የምግብ ርዳታ ያቋረጠው ለችግረኞች መከፋፈል ይገባው የነበረ እህል በተደጋጋሚ በመዘረፉ እና በመሸጡ ነው ። በዚህ ጉዳይ ዙርያ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት በትግራይ ክልል አደጋ መከላከል ኮሚሽን የአስቸኳይ ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገብረእግዚአብሔር አረጋዊ፦ የዓለም የምግብ ድርጅትን ጨምሮ ሌሎች ተቋማት የሚያቀርቡትን የምግብ ድጋፍ ካቋረጡ 20 ቀናት እንዳለፈ ጠቁመዋል ። በትግራይ ክልል የርዳታ እህል በተደጋጋሚ ስለመዘረፉም ተናግረዋል ። ክልሉ በተለያዩ ኃይሎች እየተዳደረ መሆኑን በመግለጽም ለዝርፊያው የውጭ ኃይሎች እጅ አለበት ብለዋል።

በመቐለ ከተማ ገበያዎች በትግራይ ክልል የማይከፋፈል የዓለም ምግብ ድርጅት አርማ ያላቸው የምግብ አይነቶች ጭምር ሲሸጡ እንደሚስተዋል ግን ጠቁመዋል ...

ዘገባ፦ሚሊዮን ኃይለሥላሴ ከመቐለ፤ ዶይቸ ቬለ (DW) https://www.facebook.com/dw.amharic/posts/pfbid0uhwFKg7M3pacxiFeSLTQwHytUxkbmbQGyWKz6GK5ok95VzT67PBEzdyddZhGvVZbl
3.8K viewsDW Amharic, 15:19
Open / Comment
2023-05-03 17:40:07
በዓለም ዙሪያ ከሩብ ቢሊዮን በላይ ሰዎች በ2022 ተርበዋል

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም መርኃ ግብር ዛሬ ይፋ ባደረገው «የ2023 የዓለም የምግብ ቀውስ ሠነድ» መሰረት ከስድስት ወራት በፊት በተደረገ ጥናት በዓለም ዙሪያ 258 ሚሊዮን ሰዎች ተርበዋል ። የዓለም አቀፍ ድርጅትቱ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ፦ «ከሩብ ቢሊዮን በላይ ሰዎች ለብርቱ ረሐብ ተጋልጠዋል፤ እንደውም ከፊሉ ወደ ጠኔ አፋፍ ተጠግተዋል» ሲሉ ተናገግረዋል ። እንደ ድርጅቱ መግለጫ ከሆነ፦ በዓለም ዙሪያ በ58 ሃገራት የሚገኝ ከሩብ ቢሊዮን በላይ ሕዝብ በጎርጎሪዮሱ አቆጣጠር 2022 ለአጣዳፊ የምግብ ዋስትና እጦት ተጋልጦ ቆይቷል ።

ከተጠቀሰው አሐዝ ከዐርባ በመቶ በላይ ብርቱ የምግብ ችግር ያጋጠመባቸው ተብለው ከተጠቀሱ አምስት ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ ትገኝበታለች ። የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፤ አፍጋኒስታን፤ ናይጄሪያ እና የመንም በየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠነድ ከተጠቀሱት ሃገራት ይገኙበታል ።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በአውሮጳ ኅብረት የተቋቋመው የሰብዓዊ ድርጅቶች ኅብረት የዓለም የምግብ ቀውሶች ዘገባ እንዳመለከተው በጎርጎሪዮሱ አቆጣጠር 2022 በሶማሊያ፣ በአፍጋኒስታን፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ሄይቲ፣ ናይጀሪያ ፣ደቡብ ሱዳንና የመን ደግሞ ሰዎች ለሞትና ለጠና ረሃብ ተዳርገዋል ። በጎርጎሪዮሱ አቆጣጠር 2022 ከኢትዮጵያ እና ከዚምባብዌ ግን ሙሉ መረጃ አለመገኘቱንም ሠነዱ ይጠቅሳል ።

የምስል መረጃ፦ የ2023 የዓለም የምግብ ቀውስ ሠነድ
3.8K viewsDW Amharic, 14:40
Open / Comment
2023-05-03 16:33:56
ኦሮሚያ ክልል በደቦ ፍርድ ኢሰብአዊ ድርጊት ፈጸሙ የተባሉ ተያዙ

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ ሃርወዩ በምትባል ቀበሌ ሁለት ወጣቶች ላይ ኢሰብአዊ ርምጃ የወሰዱ የተባሉ ባለስልጣናት መታሰራቸው ተገለጸ ። በአከባቢው ሰሞኑን ሁለት ወጣቶች እጅ እግራቸውን የፊጢኝ ወደኋላ ታስረው ሲደበደቡና ሲሰቃዩ የሚያሳይ ምስል በማኅበራዊ መገናኛ ተለቅቆ መነጋገሪያ ሆኗል ። ጃሮ ዳሌ እና ጋርቦሌ ዋቆ በተባሉ ሁለት ወጣቶች ላይ የተፈፀመው የደቦ ፍርድ በሚል በሰብአዊ መብት ጥሰት ተተችቷል ።

የያቤሎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጎቡ ጫና በተለይም ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት፤ በዚህ ሰብአዊ መብትን በጣሰው ድርጊት የተሳተፉት ከቀበሌ አስተዳዳሪ እስከ የአከባቢውን ሰላም እንዲያስጠብቁ የታጠቁ ሚሊሻዎች ያሉት ናቸው ብለዋል ።
በመሆኑም ወጣቶቹን ይዘው ያለ ፍርድ አስረው በማሰቃየት ድርጊት የተጠረጠሩ እስከ ዛሬ የቀበሌ አስተዳዳሪ እና ታጣቂ ሚሊሻዎችን ጨምሮ ዐሥር ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ለፍረድ እየቀረቡ ነው ሲሉ ገልፀዋል ።

አንደ ኃላፊው ገለጻ ለችግሩ መነሻ የሆነው በቀበሌው 6 ኩንታል የርዳታ እህል ጠፍቶ በገበያ መሸጡና በዚህም ስርቆት ሁለቱ ወጣቶች መጠርጠራቸው ነው ። ሁለቱ ለድብደባ እና ስቃዩ የተዳረጉት ወጣቶች አንዱ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ እረኛ ነው ተብሏል ።

የወረዳው አስተዳዳሪ ድብደባው የተፈፀመባቸው ሁለቱ ወጣቶች አሁን በደህና ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙና እነሱን የሚያስከስስ መረጃ አለመኖሩንም አንስተዋል ።
ስለጉዳዩ የተጠየቀው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ መረጃ እያሰባሰብኩ ነው ብሏል፡፡

ዘገባ፦ሥዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ፤ ዶይቸ ቬለ (DW)
4.1K viewsDW Amharic, 13:33
Open / Comment