🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

DW Amharic

Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic D
Logo of telegram channel dw_amharic — DW Amharic
Channel address: @dw_amharic
Categories: News
Language: English
Subscribers: 42.70K
Description from channel

ይህ የዶይቼ ቬለ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። ትኩስ ዜና፣ በአበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ትንታኔ ያቀርባል።

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages 590

2021-02-06 19:57:15 ቀጣዩን የሶማሊያ ምርጫ በሚመለከት በተከፋፈሉት የፖለቲካ መሪዎች መካከል የተደረገው አስቸኳይ ውይይት ያለ ስምምነት መጠናቀቁን የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አስታወቁ። ሚኒስትር ኦስማን አቡካር ዱቤ ዓርብ ማምሻውን ሞቃድሾ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ « መንግሥት በአከራካሪ ጉዳዮች ላይ ለመደራደር እና እልባት ለመስጠት ሀሳብ ያቀረበ ቢሆንም አንዳንድ ማስተዋል የተሳናቸው ወንድሞቻችን ግን ጉዳዮቹን ለመፍታት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል» ብለዋል።
በሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት እና በፌዴራል መንግሥታት መካከል በምርጫ ሂደት ላይ ለቀናት የተደረገው ድርድር እልባት ሳያገኝ ትናንት መጠናቀቁ ምናልባትም ለፊታችን ሰኞ በተቆረጠው ቀነ ገደብ መሠረት ሶማሊያ ውስጥ አዲስ ፕሬዝደንት መምረጥ አይቻል ይሆናል ተብሏል።
ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ እና የሶማሊያ አምስት የክልል አመራሮች እ.ጎ.አ. መስከረም 17 ቀን በ 2020 መገባደጃ እና በ 2021 መጀመሪያ ላይ መንገድ የሚከፍት የፓርላማ እና ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲካሄድ ከስምምነት ደርሰው ነበር። ይሁንና ይበልጥ በቅፅል ስማቸው ፋርማጆ በመባል በሚታወቁት ፕሬዚዳንት እና በአንዳንድ የክልል ተቀናቃኞች መካከል አለመግባባቶች እየተባባሱ በመምጣታቸው ይህ ስምምነት ሊፈርስ ችሏል። ለሁለተኛ ጊዜ የፕሬዝዳንትነት ቦታ የሚፈልጉት ፋርማጆ ዛሬ ሌላ ስብሰባ በፓርላማ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
3.8K viewsDW Amharic, 16:57
Open / Comment
2021-02-06 19:56:26 https://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8B%B5%E1%88%9B%E1%8C%AE%E1%89%BD-%E1%88%9B%E1%88%85%E1%8B%B0%E1%88%AD/av-56482161
3.8K viewsDW Amharic, 16:56
Open / Comment
2021-02-06 19:56:08 የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት ወደ አንዳንድ የሰሜንና ሰሜን ምዕራብ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚያደርጋቸውን በረራዎች ከትናንት ከሰዓት በኋላ አንስቶ ማቋረጡን አስታወቀ። አየር መንገዱ ወደ ባሕር ዳር፣ ጎንደር እና ላሊበላ የሚያደርጋቸውን በረራዎች የአየር ሁኔታው እስኪስተካከል ድረስ ማቋረጡን ያስታወቀው በይፋዊ የፌስ ቡክ ገፁ ነው። በኢትዮጵያ ሚትዮሮሎጂ አገልግሎት የትንበያ ባለሙያ የሆኑት አቶ ጥላሁን ውቤ ለአየር ሁኔታው ምክንያት ከሱዳን አካባቢ ያለው ከፍተኛ የሙቀት ግፊት የፈጠረው ችግር ከሱዳን የሚነሳ አቧራ አምና እና ካች አምናም ተመሳሳይ የበረራ መስተጓጎል ፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።
3.8K viewsDW Amharic, 16:56
Open / Comment
2021-02-06 19:55:41 https://p.dw.com/p/3ozMM?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
3.9K viewsDW Amharic, 16:55
Open / Comment
2021-02-06 19:54:47 የአፍሪቃ ሕብረት መሪዎች ለሁለት ቀናት የሚዘልቅ ውይይታቸውን ዛሬ በኢንተርኔት ማካሄድ ጀምረዋል። መሪዎቹ አህጉሪቱን በሚመለከቱ የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ጉዳዮች እና በወረርሽኙ ምክንያት ችላ የተባሉ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በዋናነት እንደሚወያዩ ተገልጿል። የዘንድሮው የመሪዎች ጉባኤ የተጀመረው ግብፅ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በሽታው በአፍሪቃ መገኘቱ ከተረጋገጠ ከአንድ ዓመት ገደማ በኋላ መሆኑ ነው። ወረርሽኙ በአህጉሪቱ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትል ይሆናል በሚል ተሰግቶ የነበረ ቢሆንም ከሌሎች የዓለም ክፍሎች ጋር ሲነፃፀር በሽታውን ጥሩ በሚባል ደረጃ አፍሪቃ መቋቋሟ ተገልጿል። የአፍሪቃ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል (ሲዲሲ) እንደሚለው በዓለም ላይ በተህዋሲው ከተያዙት 3,5 በመቶ ያህሉ ብቻ ናቸው ከአፍሪቃ። በበሽታው ወይም በከሽታው ጋር በተያያዘ ሕይወታቸው ካለፉትም ቢሆን በአፍሪቃ የተመዘገበው አራት በመቶ ነው። እንዲያም ሆኖ በርካታ የአፍሪቃ ሃገራት የኮቪድ 19 ክትባት የሚያገኙበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ ይገኛሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም ላለፈው አንድ ዓመት የአፍሪቃ ሕብረት ሊቀመንበር ሆነው ያገለገሉት የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንት ስሪል ራማፎዛን በመተካት የዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ቺሴ ኬዴ በይፋ ሥራቸውን ለመጀመር ተሰይመዋል። ራማፎዛም ዛሬ ከወንበራቸው በመነሳት ሥልጣኑንን አስረክበዋል።
« የሕብረታችንን ባንዲራ ለፕሬዚዳንት ቺሴ ኬዴ እያስረከብኩ ህብረታችንን ለመምራት ለሚወስዱት ኃላፊነት መልካሙን ሁሉ እመኝላቸዋለሁ።»
ከዚህም ሌላ የአፍሪቃ ሕብረት አባል ሃገራቱ በ34ተኛ ጉባኤያቸው የቀድሞው የቻድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙሳ ፋኪ ማህማትን ዳግም የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር አድርገው መርጠዋል።
4.7K viewsDW Amharic, edited  16:54
Open / Comment