Get Mystery Box with random crypto!

. . .ልበረታ ብርታቷን እየፈተንኩ ነበር። የሂወት ጭነቷን ተጭና በመንገዷ ነበረች ፣ እኔ ደሞ | ቅኔ ያለው ትውልድ

. . .ልበረታ ብርታቷን እየፈተንኩ ነበር።

የሂወት ጭነቷን ተጭና በመንገዷ ነበረች ፣ እኔ ደሞ የሂወት ጦሯ አቁስሎኝ መታከም ፈልጌ በመንገዷ ቆምኩ . . . ጥቁር ምስኪን ነፍስ. . ትንሽዬ መለዓኬ ፣ ትልቅዬ ሴጣኗ………

በቀስታ ስትጓዝ አፈሩን ምቆጥር ትመስላለች . . . ወደራሷ ነው ምትሄደው. . . ከራስ ጋር ያለን መንገድ የተቆረጠብኝ መስሎ ተሰምቶኝ ስለነበረ የሷንም መንገድ አቋርጬ ፅናቷን ልማር ፈለኩ. .


እንደ በጋ ዝናብ ያለ ውሃ ላኩባት. . . ድንገት ነውና ጨነቃት ፣ ድንገት ሆኖብኝ ጨንቆኝ እያየሁት ነውና ስሜቷ ገባኝ……… ወደኃላ ተመለሰች ፣ ኃላዋንም በውሃ ጠብታዎች ሞላውት…………

መሬቱ ጥም የለውም . . መጦ አላጎደለላትም. . ሰማይ የባለ ደመና ተራ ነውና ፀሃይ ተኝታለች አላተነነችላትም . . . ነፍሴ በነፍሷ ስቃይ መጀገን ፈልጋለችና አራራችላትም……

እቺ ትንጥ ምስኪን በፅናቷና በድንገታዊ ፈተናዋ ማሃል ብቻዋን ቆማለች. . ወይ ሞት ወይ ሂወት?

ሰዓታት የሰበሰበችውን መብል ለውሃው መስጠት የመጀመርያዋ ግዴታ ነበር ……… ባትፈልግም አረገችው ። አይኔ እንባ እንባ አለው ፣ ለገባረችው ምግቧ አስመስዬ ለገበርኩት ክብሬ አንጠባጠብኩ።

ተፍጨረጨረኝ ጥረቷ መልስ የለውም ፣ በዚም በዛም ዝግ ነው . . . የኔ ምስኪን ትንሽዬ መውጫ ቀዳዳውን አጣችው . . . ያበላሸውትን
ላስተካክለው ፈለኩ. . ግን እንዴት እማርባታለው? እኔም ያበላሸው እስኪያስተካክለው በመጠበቅ ?………

ከሆኑ ደቂቃዎች በኃላ

አቅጣጫ መረጠጭ ፣ ገረመኝ ወደፊት ያለው መንገዷ ኃላ ካለው መንገድ በላይ በውሃ ጠብታዎች የተሞላ ነበር ቢሆንም ምርጫዋ የፊቱ ነበር. . . ደቃቃ አካሏና ፈተናዋ ጦርነት ከፈቱ ታገለችው………… ተጋገሉ. . . ጫፍ ደረሰች ፣ ጥርሴ ፈገገ …………

በመጨረሻ ወጣች . . ትንሽየዋ መልዐኬ ።

ድ . . ክ. . ድ. . ክ ብላ ወደፊት መሄዷን ገታችና . . . ድክ ድክ ብላ ወደኃ ዞረች ለደቂቃ ያለፈችውን መሰናበቷ መሰለኝ ወይም ያልገባኝን መልዕክት የነገረችኝ መሰለኝ. . . . እሷ ወደፊቷ ስትመለስ እኔ ከፈተናዎቼ ጋር እያየዋት ስሸኛት ነበር…………

<< ፈተናው ትንሽ ሆኖ አደለም ያለፍኩት
ውዴ. . . በፈተናው ልክ ጠንክሬ የተሰራው
ስለሆነ እንጂ ……… ተነሽ የተሰበረን እግር
ሚያሸው አካሉ ላይ ያለው እጅ እንጂ ሌላ አደለም>> ያለች መሰለኝ . .

ለመኖር ብዬ መኖሯን ልነጥቃት በነበረችው ትንሽዬ ጉንዳን . . ሳትሞት እድኖር አሳይታኝ እደመንገዷ በመንገዴ መራችኝ !!


…………… {#ት ዝ ታ }

@tizetawe
@tizetawe
@tizetawe