Get Mystery Box with random crypto!

'…አንድ በጣም የሚያምር ቃል ለማሰብ እስከሚያስቸግር ድረስ አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል። ይህ ቃል | ቅኔ ያለው ትውልድ

"…አንድ በጣም የሚያምር ቃል ለማሰብ እስከሚያስቸግር ድረስ አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል። ይህ ቃል እኩልነት የሚለው ነው። ጥቂት አሳቢዎች(ሃሳብ አፍላቂዎች) የሰው ልጆች እኩል ናቸው ይላሉ።... ……

ሁሉም ሰው ልዩ ነው። ገና እኩል በሆናችሁበት ቅፅበት ህዝብ ትሆናላችሁ። ግላዊነታችሁ ይወሰድባችኋል። ራሳችሁን መሆናችሁ ያከትምለት እና ማሽን ውስጥ ያለ አንድ አይነት ጥርስ ትሆናላችሁ።………

እኔ_እኩል_አለመሆንን_አስተምራለሁ ፤ ልዩ መሆንን አስተምራለሁ። እያንዳንዱ ግለሰብ ልዩ ሲሆን በልዩነቱም መከበር አለበት። እያንዳንዱ ግለሰብ ልዩ ስለሆነ ተፈጥሯዊ መብቱ < ለሰው ልጆች የልዩ መሆን እድገት እኩል መብት መሰጠት አለበት > የሚል መሆን አለበት።....

ሰው እኩል አይደለም፤ ሰው ሁሉ ልዩ ነው። እያንዳንዱ ሰውም በራሱ ዓለም እንደሆነ ተደርጎ መከበር አለበት። የሌላ የማንም ሰው የበላይ ወይም የበታች አይደለም። ልዩ ነው፤ ብቸኛ ነው። በዚህ ብቸኝነቱ ውስጥም ውበት አለ። ምክንያቱም ህዝብ ወይ ቡድን ሳይሆን ራሳችሁን ትሆናላችሁና። "

{ ባግዋን ራጅኒሽ ኦሾ ፦ ራስን መሆን}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!