Get Mystery Box with random crypto!

…………… 'ከዛጎሌ ውስጥ መውጣት ብቻ አደለም ምፈልገው. . . ዘጎል ውስጥ ሆኜም እደነበር መር | ቅኔ ያለው ትውልድ

……………

"ከዛጎሌ ውስጥ መውጣት ብቻ አደለም ምፈልገው. . . ዘጎል ውስጥ ሆኜም እደነበር መርሳት ጭምርም እንጂ " አለችኝ. .

ቆንጆ ሳይሆን ቆንጅና እራሷ ናት . . ተሰብራ እራሱ ሙሉ ምትሆን ሴት ናት ………

"የማልችለውን ተሸክምያለው እያልኩክ አደለም ፣ ምችለው ከብዶኛል እንጂ……… አሁን ህመም አለው . . ጠባሳውን እየው . . ፀጉሬን ተመልከት
፣ ተንጨባሮዋል አደል? ፣ እግሮቼን እያቸው እዴት እዳደፉ ፣ የጥፍሬን ቆሻሻዎች ተመልከት ፣ የሰውነቴን ጠረን ምን እደሚል አፍንጫክን ጠይቅ. . . ስለማይታየው የውስጤ ህመም ምስክር ናቸው………… " ብሷቷ ንግግሯን ገታው………

ፀጉሯን ፣ እግሯን ፣ ጥፍሯን ቀስ በቀስ ከዚህ በፊት እደማያቃቸው ሰው አየዋቸው . . . . . ምንም ሆና ውበት ናት !

"አልጋዬ የእሾህ አልጋ ፣ ምመገበው ምግብ የሰው የሰው ስጋ ፣ የምጠጣው ውሃ ደም ደም ይመስሎኛል. . . ለምን መሰለክ ? ውስጤ በቀልን የተጠማ ስለሆነ ነው"

በሃሳባዊ ሃዘኔ ውስጥ ይችን ውብ የማር አበባ ስለቀጠፈው ንፋስ አስባለው . . . ከዚህ በኃላ ቅዝቃዜን ጠልታ ስለምትሰቃይባቸው ሞቃት ወቅቶች ተክዛለው……

"ስለፈሰሰው ደሜ ደም ፈልጋለው ስለተንገላታው ስጋዬ ስጋ እሻለው . . በስለት ስለተቆራረጠው ነፍሴ ነፍስ ከጅላለው. . ይሄን ሚመልስልኝ አለ ? "

ውስጧ ሲወራጭ ይሰማኛል . . እደታረደች ወፍ ትፈራገጣለች. . . ያለችውን ምጠይቅበት ደረጃ እዳደርስ ባረግ ብዬ እመኛለው. . ግን ምኞት ነው. . . ለዛሬ ማዳኛ መድሐኒት ኬት ላምጣ ?

"ከመውደቁ በፊት ከፍ ከፍ ያለ የሰው ልብ ነው
ያረደኝ . . .ሳይከብር የተዋረደ . . አሁን እኔ የነጠፈ ደረቅ የውሃ ጉድጓድ ሆኛለው . . መጦኛላ!

ገና ምንጭ ናት እኮ . . . . በውብ ለምለም ቄጤማዎች መሃል የተደበቀች ጣፋጭ ምንጭ፣
እዲህ ብዬ ልነግራት ፈልጋለው ግን ደሞ ፈራለው. . !

"በፍርድ ጊዜ እውነትን አራቁብኝ ፣ ገልገበው እርቃኔን አስቀሩኝ ፣ አእምሮዋቸው ጎሎዋልና እንዴት ልቻላቸው ? ለቀሚሴ መቀደድ ለሷ መጨቅየት . . ተገላቢዋ እኔ እያለው ለገላቢው ወግነው ቆሙ . . . ለነዚህ ፍጡር እጄ ስለት
ብታነሳ ምኑ ጋር ነው ሃጥያቴ ?"

አሳዘነችኝ ፣በበቀልና በምህረት መሃል ያለችን ነፍስ እደማየት ያለ ህመም ይኖር ይሁን . . . ?

ቀስ ብዬ ተጠጋዋት ፣ ሸሸችኝ . . ጠተጋዋት ሸሸችኝ . . .

"እፈራችዋለው ፣ የአይኖቼ ብሌን ስለእናንተ ጨለማን ያያል . . እራሴን ለቦዘኔነት ሳልሰጥ
ነው የተዋረድኩት. . ምድረ በዳ ሆኛለው !"

አይኖቿ እንደ ርግቦች ናቸው . . ያለችው ጨለማ የለም ፣ሮማንና የጣፈጠ ፍሬ ፣ከሽቱ ሳር ጋር ያለባት የገነት መንገድ ናት! በሱፍ አበባ መሃል እደሚሰማሩ እንደሚዳንቆ ግልገሎች ገና ብቅ ብቅ ያሉ የልጅነት ሃሎች አሏት . . እንዴት ብዬ ስትነድ አያታለው ?

አሁን ላቅፍት አላሰብኩም ከዚህ በኃላ መች እደማስብም አላውቅም ግን አብርያት ታምሜ አብርያት ልድን ወስኛለው!

{#ት ዝ ታ }

@tizetawe
@tizetawe
@tizetawe