Get Mystery Box with random crypto!

……… «እየው እጄ ሞቶ፤ እየው እግሬ ሞቶ ያስለፈልፈኛል ሆዴ ብቻ ቀርቶ» ሺህ ሰዎች ተሳስተው | ቅኔ ያለው ትውልድ

………

«እየው እጄ ሞቶ፤ እየው እግሬ ሞቶ
ያስለፈልፈኛል ሆዴ ብቻ ቀርቶ»

ሺህ ሰዎች ተሳስተው አንዱ ብቻ ልክ ሊሆን ይችላል ... አዎን መቶ አህዮች ባንድነት ሲያናፉ ከአንድ መሲንቆ የተሻለ ጣዕም ሊኖራቸው አይችልም። አሁንም ቢሆን እኔ የማምነው ከብዙ ምላስ በትንሽ ስራ ነው።

ኢትዮጵያ እጆቿን ወደሰማይ ዘርግታ ፀሎት ስታደርስ በቀለም ትምህርት ናላው ሰክሮ በእጁ መስራት ከማይፈልግ ትውልድ አድነኝ ሰውረኝ ብላ መለመን አለባት።

አእምሮ ያሰበውን ያንን ስራ ላይ እጅ ማዋል አለበት። በእጅ አማካይነት በስራ ያልተገለጠ ሃሳብ የማይታይ፤ የጋን መብራት ሆኖ ይቀራል። እርግጥ ዓለም በሃሳብ ባህር የሚዋኙ መለኮት የሚታያቸው ሰዎች ያስፈልጓታል። ያለእነርሱ ወደፊት ልትራመድ አትችልም። ይሁን እንጂ የአክሱም ሀውልቶችና የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የታነፁት በህልም ብቻ አይደለም። በእጅ ነው። የፖለቲካ ፍልስፍናን በመለፈፍ ብቻ ኢትዮጵያን እናሻሽላለን ማለት ዘበት ነው። የመንፈስ ደካማነት ምልክት ሊሆን ይችላል። ምላስን ከማወናጨፍ ይልቅ እጅን ለትንሽ ስራ መዘርጋት የበለጠ ወኔን፤ ቆራጥነትንና መስዋእትነትን ይጠይቃል።

አእምሮን የሚመራው እጅ ነው ማለቴ አይደለም። እጅ ለስራ እንዲቃጣ የማያደርግ አእምሮ ህሊና ቢስ ነው።

እምነትና ድርጊት ከተለያዩ ምሠሶው በምስጥ እንደተበላ ቤት መዛግ ከዚያም መፍረስ ይመጣል - ወና ቤት መሆን።

{የህሊና ደወል _ ከበዓሉ ግርማ}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!