Get Mystery Box with random crypto!

' ትዝታሽን ፡ ለእኔ ትዝታዬ ፡ ለአንቺ...ገጽ 47-48 | ቅኔ ያለው ትውልድ

<<…የምድር ስፋት ሞታችንን ኢምንት አድርጎታል። ማልዶ የሚሰማው መርዶ ዱብ ዕዳነቱ ለሟች ቤተሰብ ብቻ ነው። ሟች በሄደ ጊዜ...ሕይወት በሚወዱት ሰዎች ዘንድ ትቀዘቅዛለች። በቀሪው ዓለም ግግር በረዶ የሚያቀልጥ ነዲድ ፀሐይ እጁን ይዘረጋል። ሕይወት ሞቆ ይቀጥላል። የማናውቀው ሰው ሞት አያስገርመንም። አይከብደንም። ብዙ ሰዎች በከባድ ሕመም ውስጥ እንዳለፉ የምንረዳው ሞት ቅጥራችንን አልፎ ቤተሰባችንን፥ የእኛ የምንለውን ሰው በጎበኘ ጊዜ ነው። ያኔ....የማጽናናት ቃል ለልብ ጠብ እንደማይል እንታዘባለን።

ጊዜና ትዝታ ነን። ቆዳችን ስባችንን ብቻ ሳይሆን የኖርነውን ጊዜ ትዝታ ጭምር ነው የጋረደው። በዓይን ስንታይ አሁንን ነን። ነገር ግን ዓመታትን በልተናል። በደማችን ውስጥ የሚርመሰመሰው ዥንጉርጉር ትዝታ ነው። ያለፈውን ጊዜ፣ ያለፈውን ስሕተት ወደ ኋላ መልሶ የሚያስተራርም አዳኝ ልዕለ ሰብእ የለንም። ሆኖም ሰዎች ነን። በዚህ ምድር ላይ ሰው ሆነን ስንኖር ይህ የመጀመርያችን ነው? አናውቅም። ትውስታው የለንም። ወደ ኋላ መመለስ ቢቻል ብለን እናልማለን። ሕልሞቻችን በሕዋው ላይ ይተምማሉ። ተስፋዎቻችንም በሰማያት ላይ ይዳምናሉ። ስለፍቅር ብዙ መሥዋዕትነት ከፍለናል። ስለሰላምም ጦርነት ዘምተናል። አሁን ድረስ ልክነቱን አናውቅም። ቢያልፍም ጮክ ብለን የምንናገረው ጸጸት የለንም። ስለሞቱት ስንል፥ ስለከፈልንውም መሥዋዕትነት ስንል ዝም ማለትን እንመርጣለን። ...>>

" ትዝታሽን ፡ ለእኔ ትዝታዬ ፡ ለአንቺ...ገጽ 47-48


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!