Get Mystery Box with random crypto!

………………………………………… የማለዳ እንጉርጉሮ ………………………… አንዳንዴ ደሞ ጎ | ቅኔ ያለው ትውልድ

…………………………………………
የማለዳ እንጉርጉሮ
…………………………

አንዳንዴ ደሞ ጎህ ቀዶ
አብሮኝ ያደረው ደወል ፤ ከራስጌየ ተጠምዶ
ከወፎች ቀድሞ ሲያመጣልኝ “ ነግቶብሃል” የሚል መርዶ
ብትት ብየ፤ ደንብሬ
ግማሸ ፊቴን ትራሴ ውስጥ ቀብሬ

“ እኮ ዛሬም እንደወትሮ
ካውቶብስ ወደ ቢሮ
ከኬላ ወደ ኬላ
ዛሬም በግንባሬ ወዝ ልበላ
አሺ ከዚያስ በሁዋላ?”

እያልሁ ልቤን ስሞግት ፤ መልሱን አያመለክተኝ
ይሄን ያህል ነው የታከተኝ፤

ጉዞየ፤ ካዋላጅ እቅፍ፤ እስከገናዦች አልጋ
ባራት አግር ተጀምሮ፤ ባራት ሰው ሸክም እስኪዘጋ
መንገዱ መንገድ እየሳበ
ትንንሹ ዳገት ፤ለትልልቁ እያሰረከበ
እንደ ሀረግ ስጎተት፤ እንደ ጥንቸል ስፈጥን
“ምን ሽልማት ታሰበልኝ? ይህ ልፋቴን የሚመጥን
እያልሁኝ ሳውጠነጥን፤

አንዳንዴ ደሞ ሲመረኝ
እንደ ለማዳ ፈረስ፤ ሞትን በፉጨት መጥራት ሲያምረኝ፥
ዛፉን የተቀማ አሞራ
በኮረንቲ ምሶሶ ላይ፥ ጎጆው ባዲስ መልክ ሲሰራ
ማርዋን የተዘረፈች ንብ ፤ በየአበባው ስትሰማራ
አይና
እንዲህ እንዲህ እላለሁ፤ ርስ በራሴን ሳጽናና፡ -

ሺህ ጊዜ ብትራቀቅ ፤ ቃላት መርጠህ ብትገጥም
ከዚህ አሞራ አታንስም ከዚች ንብም አትበልጥም
ተፈጥሮ ትግልን እንጂ፤ የድል ዋስትናን አትሰጥም
ቻለው! "


{በእውቀቱ ስዩም}


╭•❀|❀:✧๑♡๑✧❀|❀:
@keney_serezoch
@keney_serezoch
╰ೋ•✧๑♡๑✧•ೋ

ፍቅር አሁን !!