Get Mystery Box with random crypto!

Merahit Club / መራሒት ክበብ

Logo of telegram channel merahitclub — Merahit Club / መራሒት ክበብ M
Logo of telegram channel merahitclub — Merahit Club / መራሒት ክበብ
Channel address: @merahitclub
Categories: Uncategorized
Language: English
Subscribers: 1.73K
Description from channel

A University based women empowerment club found in Hawassa University.
መራሒት የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም መሪ ሴት ማለት ነው።
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ከታች ባሉት username ያሳውቁን
@teq_uam
@Meron_Deribe
@merahitclub
@Merahitbot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 5

2022-01-14 21:42:02
#FinalExam

Computer Programming (C++) last year Final Exam


ለአስተያየት ፣ ለጥቆማ አልያም ለጥያቄ
@amharictutorialclassbot

ትምህርት ነክ መረጃ ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@amharictutorialclass
@amharictutorialclass
129 views18:42
Open / Comment
2022-01-14 21:42:02
Debre tabor unversity
Civics mid Exam

@atc_edu
@amharictutorialclass
@amharictutorialclassbot
118 views18:42
Open / Comment
2022-01-14 21:42:02
Debre tabor unversity
Civics mid Exam

@atc_edu
@amharictutorialclass
@amharictutorialclassbot
111 views18:42
Open / Comment
2022-01-10 16:12:57 https://socialmovementtechnologies.org/internet-access-protection-and-using-petitions-strategically-for-people-power-series/
94 views13:12
Open / Comment
2022-01-03 23:51:09
ትችያለሽ ...

#መራሒት
#እኔ_የእህቴ_ጠባቂ_ነኝ
@merahitclub
102 views20:51
Open / Comment
2022-01-02 17:38:00
እኛ ማነን

@merahitclub
152 views14:38
Open / Comment
2021-12-31 23:52:40
የዛሬዉ የመራሒት ፕሮግራማችን እጅግ ባማረና በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።ለተሳተፋችሁ ሁሉ እጅግ በጣም እናመሰግናለን !!

#መራሒት
#እኔ_የእህቴ_ጠባቂ_ነኝ
@merahitclub
366 views20:52
Open / Comment
2021-12-31 10:12:33
ሠላም መራሒቶች

እንደምን ቆያችሁን!! ዛሬም እንደተለመደው ለzero plan ምሽታችን ይሆን ዘንድ ከዚህ በፊት ከሰራናቸው ዝግጅቶች በአይነቱ ለየት ያለ አስተማሪ ፕሮግራም ይዘንላቹ መተናል። በአሁኑ የzero plan ምሽታችን ሴቶችና ያልተደፈሩ ሙያዎች በሚል ርዕስ ቆንጆ ምሽት ልናሳልፍ ወደድን!

በዝግጅቱም ሰፋ ያለ ውይይት
ጥያቄ እና መልስ
ሙዚቃ
ማራኪ ገፅ
እንዲሁም ስለ ፈላስፋዋ ሃይፓትያ የምንለው ይኖረናል።

ስለዚህም አርብ ከምሽቱ 1:30 ላይ white house በሚገኘው zero planአችን ተገናኝተን ቆንጆ ጊዜ እናሳልፍ ዘንድ ጋብዘናል።

መቅረት አይታሰብም

#merahit
#i_am_my_sisters_keeper
@merahitclub
71 viewsedited  07:12
Open / Comment
2021-12-30 12:31:30 የሰሞኑ ጉንፋን!

የሰሞኑ ጉንፋን ለየት የሚያረገው ከፍተኛ ትኩሳት እና ጠንከር ያለ ሳል አለው በተጨማሪም እነዝህ ምልክቶች ይታዩበታል:-

• ብርድ ብርድ ማለት
• የመገጣጠሚያ ህመም
• የጀርባ ህመም
• የጡንቻ ህመም
• ምግብ ፍላጎት መቀነስ
• ኃይለኛ ራስ ምታት
• ፍዝዝ ማለት

ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል ?

ጉንፋን ዋና መንስኤዎቹ በትንፋሽ በሳል እና በማስነጠስ የሚተላለፉ ቫይረሶች ናቸው። ለምሳሌ÷ ኮሮና ቫይረስ ፣ራይኖ ቫይረስ፣ ኢንፍሉዌንዛ አዴኖ ቫይረስ እና የመሳሰሉት ጉንፋንን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የሰሞኑ ጉንፋን ኮሮና ይሁን አይሁን የሚታወቀው በምርመራ ብቻ ነው። ስለዚህ ምን እናድርግ?

• የመከላከያ መንገዶቹን ይተግብሩ
• ሁሌም የአፍ እና አፍንጫዎን ይሽፍኑ
• የእጅ እና አካል ንክኪ ይቀንሱ
• ሰዉ የሚሰበብበት ቦታ አይገኙ
• ስያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫዎን በክንድዎ/በጨርቅ ይሸፍኑ
• መንግስት በነፃ ያቀረበውን የኮሮና ክትባትን ይውሰዱ

ለልጆች እና ህፃናት የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው?

• ለብ ያለ ዉሃ ዉስጥ ትንሽ ጨው አርጎ አፍንጫቸው ቀዳዳ ዉስጥ 2 ጠብታ ማድረግ በመቀጠል የአፍንጫ ቀዳዳዎችን በመምጠጫ ማጽዳት
• ትኩሳትን የሚቀንስ መድሃኒት መጠቀም ፣
• ትኩስ ትኩስ ነገሮችን ማጠጣት
• ተጨማሪ ምግቦችን በደንብ መመገብ
• የሕፃኑን ክፍል በደንብ ማፅዳት ማናፈስ
• ቤቱን በውሀ እንፋሎት ማጠን
• ንፍጥ እና ትኩሳት በጣም አስፈላጊ ፈሳሾችን እና ንጥረ ነገሮችን ይዘው ስለሚወጡ ተጨማሪ ፈሳሽ ነገሮችን ማግኘት ይኖርባቸዋል።

ለታዳጊ ህፃናት እና ለአዋቂዎችስ የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው ?

• ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ራስን በአንድ ክፍል ማግለል
• ትኩስ ፈሳሽ ነገሮችን ደጋግሞ መውሰድ
• ነጭ ሽንኩርት ማር እና ዝንጅብል መጠቀም
• በቂ እረፍት ማድረግ
• የትኩሳት እና ራስ ምታት ማስታገሻ መውሰድ
• እነዚህን መፍትሄዎ እያረጋችሁ ምንም ለውጥ ከሌለው እና ሳሉ የመባስ ትኩሳቱ የመጨመር ባህሪ ካለው ወይም ትንፋሽ የማጠር ምልክት በህፃንም ሆነ በአዋቂ ላይ ካለ በአፋጣኝ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል፡፡

ዶ/ር ፋሲል መንበረ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር እና የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም

Credit : ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ

#Health_Team
#iammysisterskeeper
@merahitclub
953 views09:31
Open / Comment
2021-12-24 15:21:47
ሰላም ዉድ የመራሒት ቤተሰቦች
እነሆ መራሒት ተወዳጁን የአርብ ምሽት ፕሮግራሟን ወደ እናንተ ለማቅረብ ዝግጅቷን አጠናቃ ምሽታችሁን ከእኛ ጋር ሁኑ ትላለች ።
ራስን ማወቅ ምንድን ነዉ?አንድ ሰዉ ራሱን አዉቋል የሚባለዉ መቼ ነዉ?በሚል ርዕስ በተሰናዳዉ ፕሮግራማችን ኑ በጋራ ደማቅ አርብ ምሽትን እናሳልፍ!!

አርብ ምሽት በቤተ-መራሒት:-
ስለ ራስን ማወቅና ባህሪያቶቹ ማብራሪያ ይሰጣል
ግጥም
አጭር ዉይይት
አዝናኝ ጨዋታዎች
የሳምንቱ መፅሐፍ
ሙዚቃና ሌሎችም አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞች የእናንተን መምጣት ይጠብቃሉ።
ዛሬም አልቀርም....እግሮች ሁሉ ወደ መራሒት zero plan ያቀናሉ

አድራሻ : 309 በሚገኘዉ zero plan

ምሽት 1:30 ማንም አይቀርም።
ኑ ምሽታችንን በጋራ እናሳልፍ...

#መራሒት
#እኔ_የእህቴ_ጠባቂ_ነኝ
@merahitclub
101 viewsedited  12:21
Open / Comment