🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)

Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት) S
Logo of telegram channel nationalexamsresult — STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
Channel address: @nationalexamsresult
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 41.40K
Description from channel

የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 3

2023-12-09 12:47:13
የኢትዮጵያ አየርመንገድ አቪዬሽን ዩንቨርስቲ ከ600 በላይ በተለያዩ መስኮች ያስለጠናቸውን ተማሪዎችን በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

በዛሬው የምርቃት ፕሮግራም በአውሮፕላን አብራሪነት በአውሮፕላን ጥገና እና መስተንግዶ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

በምርቃት ስነስርዓቱ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና ስር አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰውን ጨምሮ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት አቶ ካሴ ይማም የተማሪዎች ወላጆች በተገኙበት በኢትዮጵያ አየርመንገድ ውስጥ ፕሮግራሙ እየተካሄደ ይገኛል።

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
12.6K views09:47
Open / Comment
2023-11-16 20:12:16
በአማራ ክልል በጸጥታ ችግር ምክንያት የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ የዓመቱን የመማር ማስተማር ሒደት ለማሻሻል ጥናት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በክልሉ ምስራቅ፣ ምዕራብ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች እስካሁን ትምህርት አለመጀመሩን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ለአሚኮ ተናግረዋል። 

በጸጥታ ሥጋት ምክንያት ከተገለፁት ዞኖች ውጭ በሚገኙ የክልሉ አካባቢዎች 60 በመቶ የአንደኛ ደረጃ እና 55 በመቶ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ብቻ በመማር ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በየጊዜው ሰላም በሚኾንባቸው አካባቢዎች ከጸጥታ መዋቅሩ እና ከማኅበረሰቡ ጋር በመቀናጀት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ እየተሠራ ነው ብለዋል።

የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ ቢሮው የዓመቱን የትምህርት ሥርዓት እንደገና ለማሻሻል ጥናት እያደረገ  እንደሚገኝም ኃላፊዋ ጠቁመዋል።

በተለይ በዚህ ዓመት የክልል እና ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ የ6ኛ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የባከኑ ጊዜያትን በልዩ ሁኔታ ለመሸፈን ከመምህራን እና ርዕሰ መምህራን ጋር ውይይት እየተደረገ መኾኑን ገልጸዋል፡፡

አሚኮ

⊰  ㅤ    ⫹⫺ㅤ     ⎙ㅤ     ⌲ ⊱
࿙ ᴸⁱᵏᵉ    ˢᵘᵖᵖᵒʳᵗ    ˢᵃᵛᵉ     ˢʰᵃʳᵉ ࿚

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
13.2K viewsedited  17:12
Open / Comment
2023-11-09 14:42:19
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ነባር የመጀመሪኛ ዲግሪ አንደኛ ዓመት (Freshman) ወይም በ2015 ዓ.ም መደበኛ የሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ህዳር 06 እና 07 /2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በመሆኑም በተጠቀሱት ቀናት ብቻ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

ወደ ተቋሙ ስትሔዱ የስፖርት ትጥቅ፣ አንሶላ እና ጉርድ ፎቶግራፍ ልትይዙ እንደሚገባ ዩኒቨርሲቲው አስታውሷል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፦ regi@jju.edu.et / info@jju.edu.et
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
13.0K viewsedited  11:42
Open / Comment
2023-08-29 10:57:47
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን የሚቀበልበት መስፈርት እንደሚከተለው ይሆናል፡-

1. እንደማንኛውም ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ወጪያቸውን በመንግስት የሚሸፈንላቸውን ተማሪዎችን ፈትኖ ይቀበላል፣

2. በአሁኑ ሰዓት በማታው ክፍለ ጊዜ (Extension) በግል እየተማሩ እንደሚገኙ ተማሪዎች በመደበኛው ክፍለ ጊዜም (Regular) ተመሳሳይ ተማሪዎችን ተቀበሎ በመጠነኛ ክፍያ የሚያስተምር ይሆናል፣

3. ዩኒቨርሲቲው በፊት ከነበረው ከትምህርት ሚኒስቴር ከሚላክለት የተማሪዎች ቅበላ ውጭ በልዩነት ፈትኖ ተማሪዎችን ቢቀበልም ከዚህ በፊት በመንግስት ከሚመደብለት የተማሪዎች ቁጥር ያነሰ አይሆንም፤

4. አዋጁ በግልጽ እንዳስቀመጠው ሁሉንም የኢትዮጵያ ተማሪዎችን ታሳቢ ያደረገ የትምህርት ተቋም እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው ይገልፃል

ይሁንና በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ ድህረ-ገፆች ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሐብታሞች መማሪያ ብቻ ይሆናል ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ ሀሰተኛና የህግ አግባብነት የሌለው መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡

በመሆኑም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም ኢትዮጵያዊ መዳረሻ ፣ የእውቀት መገብያ መናኸሪያ እንዲሆን እንጂ ራስ ገዝ አስተዳደር ያስፈለገው የገንዘብ አቅም ያላቸው ተማሪዎችን ብቻ ተቀብሎ የሚያስተምር ተቋም እንዳይሆን ታስቦ እንደሆነ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ይህ ማለት አንድ ተማሪ ወደ ተቋሙ ለመማር አስቦ ሲመጣ እንደማንኛውም ተማሪ ከክፍያው በፊት የተቋሙን የትምህርት መመዘኛ መስፈርቶች (Admission paper) ሲያገኝ ብቻ ይሆናል::

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
16.4K viewsedited  07:57
Open / Comment
2023-08-28 13:26:24
በአማራ ክልል የ2016 ትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከነገ ነሐሴ 23/2015 ዓ.ም ጀምሮ ይካሔዳል፡፡

የተማሪዎች ምዝገባ እስከ ጳጉሜን 03/2015 ዓ.ም ደረስ ይከናወናል፡፡

በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች መስከረም 02/2016 ዓ.ም ይከፈታሉ የተባለ ሲሆን መስከረም 14/2016 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሥራ ይጀምራል ተብሏል፡፡

በአማራ ክልል 6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎች ምዝገባ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
12.8K viewsedited  10:26
Open / Comment
2023-08-27 12:21:49
የትምህርት ቤቶች አስተዳዳሪዎች ከአሁን በኋላ የሚመረጡት በካድሬነት ሳይሆን፣ ባላቸው ብቃትና ችሎታቸው ላይ መሠረት ተደርጎ ይሆናል።

በዚህ መሠረት በአገር አቀፍ ደረጃ በብቃታቸውና በችሎታቸው የተመዘኑ 1,600 የትምህርት አስተዳዳሪዎች ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል። ይህ ዓይነቱ አሠራር ቀጣይነት ይኖረዋል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሳደግ ሥራ በተጨማሪ የመምህራንና ርዕሳነ መምህራን ብቃትና ችሎታ ማጎልበት ትኩረት ተሰጥቶበታል፡፡

ትኩረት ካገኙ መሠረታዊ ጉዳዮች ትምህርት ቤቶችን በግብዓትና በጥራት ከማሻሻል ባሻገር ክህሎት፣ ብቃትና ችሎታ ባላቸው ርዕሳነ መምህራን እንዲተዳደሩ ማድረግ ትልቁን ድርሻ ይይዛል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል በተጨማሪ በዕውቀት ተማሪዎቻቸውን ተወዳዳሪ ማድረግ የሚችሉ መምህራንን ማብቃት ከተያዙ ግቦች መካከል አንዱ ነው።

ባለፉት 30 ዓመታት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ጥራት ወርዷል ፤ በኑሮ ለተሻሉ ደግሞ የግል ትምህርት ቤቶች የሚማሩበት ሥርዓት ተዘርግቷል።

ይህ ዓይነት አካሄድ በዜጎች መካከል በኑሮ ደረጃ ከተፈጠሩ ልዩነቶች አልፎ በትምህርት ዘርፍ ላይ መታየቱ ትልቅ ክስረት ነው። ይህ አካሄድ በአገር አቀፍ ደረጃ አደገኛ ሁኔታዎች የሚፈጥር ነው ፤ በየትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በገንዘብ ዕጦት ሳቢያ የትምህርት ጥራት ሊጓደልባቸው አይገባም።

ትምህርት የአገር የሉዓላዊነት እሴት መለኪያ ነው ፤ በዚህ ጉዳይ ለዓመታት የተቀለደበት ዘርፍ ነው አሁን እርስ በርስ መነጋገር የማይቻልበት ሁኔታ ላይ መደረሱ የችግሩ ማሳያ ነው። በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉ ከአሥር ዓመታት በኋላ ትምህርት ቤቶች እንደ አሁኑ የፀብ (የረብሻ) መፍለቂያ ሳይሆኑ የመወዳደሪያና የብቃት ማጎልበቻ ይሆናሉ፡፡

#MoE

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
13.1K viewsedited  09:21
Open / Comment
2023-08-25 21:39:45
የ8ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ተደረገ

የኦሮሚያ ክልል የ2015 የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ከክልሉ የትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የ2015 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም  ስማቸውን እና የID. ቁጥራቸውን በማስገባት ዉጤታችሁን ማየት እንደሚችሉ ቢሮው አሳውቋል።

Website:- https://oromia.ministry.et/#/result

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
12.6K viewsedited  18:39
Open / Comment
2023-07-25 08:30:51
በቅድሚያ ለ 2015 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች   እንኳን ደስ አላቹ እያልን ለተመራቂዎች ፣ ለልደት ፣ ለ Anniversary እና ለማንኛውም ዝግጅት  ምርጥ ስጦታ ከዚህ በፊት ያልተለመደ ማንኛውንም አይነት ፎቶ ወይም ምስል ባማረ ሁኔታ እንጨት ላይ በ#MDF Colour ስራዎቻችን  በተመጣጣኝ ዋጋ በሚፈልጉት Size ለወዳጅ ዘመድዎ ያበርክቱ 


ይዘዙን ያሉበት ቦታ በነፃ  እናደርሳለን!

Contact:   @Henak_21
                  0924848164

#For_More_Gifts_Package
@Habesha_Gift
2.5K views05:30
Open / Comment
2023-07-24 22:55:36 የደብረታቦር ዩንቨርሲቲ የRemedial ውጤት


በመጀመሪያ ፋይሉን ክፈቱ ከዚያም በተዘጋጀው ቦታ ላይ ሙሉ መታወቂያ ቁጥራችሁን (ID NO) በተዘጋጀው ቦታ ላይ ብቻ ጻፉ እንደ DTU16R1245:: ከዚያ ENTER ወይም NEXT ተጫኑ። ሁሉንም ውጤት እና መረጃ ማግኘት ትችላለችሁ፡፡ በገጹ ላይ የሚታየው ስም የእናንተ መሆኑን አረጋግጡ።

First open the file then Type Your full ID NO on the space provided. like DTU16R1245 . Then press enter or next. You can get all result and information. Make sure that the name displayed in the interface is yours.

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
5.8K views19:55
Open / Comment
2023-07-24 22:55:22 Jigjiga University #Remedial Program Students Results #NaturalScience


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
5.5K views19:55
Open / Comment