Get Mystery Box with random crypto!

​​#ጥቅሶች #ወንዶች : ምርጥ የፍቅር ጥቅሶች ለምታፈቅራት ሴት - ' ማፍቀር ምንም አይደ | 𝔪𝔞𝔯𝔨𝔞𝔫 🎼🎵🤪

​​#ጥቅሶች
#ወንዶች : ምርጥ የፍቅር ጥቅሶች ለምታፈቅራት ሴት

- " ማፍቀር ምንም አይደለም ፡፡ መፈቀር አንድ ነገር ነው ፡፡ ግን ማፍቀር እና መፈቀር ፣ ሁሉንም ነገር ነው። ”



- “ ለምወደው ሰው ብዙ ነገሮችን ላደርግም ላላደርግም እችላለሁ ፣ ግን ብቸኝነት እንዲሰማሽ መቼም አላደርግም ። ”



- “ አሁን ከምወድሽ በላይ ልወድሽ አልችልም ብዬ እምላለሁ ፣ ግን አንድ ነገር አውቃለሁ ነገ ከዛሬ በላይ እወድሻለሁ ። ”



- “ እመርጥሻለሁ ፣ እናም ደጋግሜ አንቺን ብቻ እመርጥሻለሁ ፡፡ ያለምንም ጥርጥር በልብ ምቴ ልክ በየ ሰከንዱ ከምንም ነገር አስበልጬ እመርጥሻለሁ ። መምረጤንም እቀጥላለሁ አላቆምም፡፡ ”



- “ ቀሪውን ሕይወቴን አብሬሽ ማሳለፍ ፈልጋለሁ ፣ ያም አሁን ቢጀምር ደስ ባለኝ ። "



- “ ስለ አንቺ እያሰብኩ ነበር ፣ እናም ለምን ያህል ጊዜ ሳስብሽ እንደነበር ማሰብ ጀመርኩ ፣ ከዛም አንድ ነገር ተገለጠልኝ ካየሁሽ ጀምሮ እስካሁን ከአይምሮዬ አልጠፋሽም ። ”



- “ በሰላም ወደ ቤትሽ እንድትመለሺ ፣ በነገሩ ሁሉ እንዲሞቅሽ ፣ ደህና እንድታድሪ ፣ እንደናፈኩሽ በነገርኩሽ ቁጥር ፣ አፈቅርሻለሁ እያልኩ እንደሆነ እወቂልኝ ፡፡ ፍቅር ቃል ሲያጣ የሌሎችን ቃላት ትርጉም መስረቅ ይጀምራል ። "



- " እኔ የበለጠ እወድሻለሁ" ስል ፣ ከምትወጂኝ በላይ እወድሻለሁ ለማለት አይደለም ። ከፊት ከሚጠብቁን መጥፎ ቀናት በላይ እወድሻለሁ ፣ በእኛ መካከል ካለው ርቀት በላይ እወድሻለሁ ፣ በፍቅራችን ሊመጣ ከሚችለው መሰናክል ሁሉ የበለጠ እወድሻለሁ ። እኛን ሊለያየን በሚመጣ ማንኛውም ነገር ባንቺ ላይ እጅ አልሰጥም ። እኔ የበለጠ እወድሻለሁ ፡፡ ”



- “ ለአንድ ደቂቃ ያህል ስላየሁሽ ብቻ : ብዙ አዲስ ምወድልሽን ነገሮች አገኛለሁ። ”

@abcdefghijknz
@abcdefghijknz
#share
#join