🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ለስራዎ ምቹ የሆነ ላፕቶፕ እንዴት ይገዛሉ? ======= በአሁኑ ወቅት ላፕቶፕ ለመግዛት ሲታሰብ ብ | Abelbeen Creative

ለስራዎ ምቹ የሆነ ላፕቶፕ እንዴት ይገዛሉ?
=======
በአሁኑ ወቅት ላፕቶፕ ለመግዛት ሲታሰብ ብዙ አማራጮች አሉ፡፡ ያሉት ላፕቶፖች በሙሉ የራሳቸው የሆነ ጥሩና መጥፎ መገለጫ ቢኖራቸውም ላፕቶፕ ሲገዙ ቢንስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መገለጫዎችመመልከት በጣም አስፈላጊ ነው

1ኛ. የስክሪን ስፋት እና
የላፕቶፕ ክብደት (Screen size and weight)
የላፕቶፕ

ስክሪን በአብዛኛው ከ9-17 ኢንች (ከ23-43 ሳንቲ ሜትር) ድረስ ይሆናል፡፡ የስክሪን ስፋቱ እየጨመረ በሄደ ቁጥር የላፕቶፑም ክብደት ይጨምራል፡፡ እዚህ ላይ ላፕቶፑን ለምን እንደሚፈልጉት ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ የላፕቶፑ መጠን እየጨመረ በሔደ ቁጥር ለማንቀሳቀስ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ከባድ ላፕቶፖችን አዘውትሮ መሸከም በሰውነታችን ቅርጽ ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ልዩ ልዩ ጥናቶች አመልክተዋል፡፡ ስለዚህ ስራችን ብዙ እንቅስቃሴ ያለበት ከሆነ ክብደታቸው አነስተኛ የሆኑና በቀላሉ ልናንቀሳቅሳቸው የምንችላቸውን መርጦ መግዛት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰፊ ስክሪን ያላቸው ላፕቶፖች የባትሪ ቆይታ ጊዜያቸው አነስተኛ ነው፡፡

2ኛ. CPU (የላፕቶፑ አእምሮ)

በአለማችን ሁለት የታወቁ የCPU አምራች ኩባንያዎች አሉ፡፡ እነዚህም Intel እና AMD ናቸው፡፡ Intel ገበያውን የተለያዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በጨመር ሲቆጣጠረው፤ AMD ደግሞ ተወዳዳሪ የሆኑ ሞዴሎችን በአነስተኛ ዋጋ ያቀርባል፡፡ እዚህም ላይ ኮምፒውተሩን ለምን ስራ እንደሚፈልጉት ማሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ የግራፊክስ ባለሙያ ከሆኑ ኤዲተር ከሆኑ ጥንድ ኮር (Dual-core CPU) ቢጠቀሙ የተሸለ የመፈጸም ብቃት አለው፡፡ ከዚህ ውጭ ለመሰረታዊ የኮምፒውተር አገልግሎት የሚፈልጉት ከሆነ ነጠላ ኮር (single-core CPU) ያለውን ላፕቶፕ ቢገዙ ከዋጋም አንጻር ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

3ኛ. RAM

ኮምፒውተርን ለመደበኛ አገልግሎት ማለትም ለቤትከሆነ ውስጥ እና ለቢሮ ወይም ለጉዞ የሚጠቀሙት ከሆነ ከ 2-4 GB ያላቸውን መጦ መግዛት የተሻለ ነው፡፡ የግራፊክ አርቲስት ከሆኑ ወይም ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ቪዲዮዎች የሚያዘጋጁ ከ4 GB እስከ 8 GB RAM ያላቸውን ላፕቶፖች መርጦ መግዛት ውጤታማ ያደርጋል፡፡

ተማሪዎች የቤት ስራቸውን ለመስራት፣ ለኢሜይል ወይም የጠለያዩ ድረ ገፆችን መጎብኘት የመሳሰሉ ተግባራትን ለመከወን ግን 1 GB RAM ያላቸውን ላፕቶፖች መግዛትም ይቻላል፡፡


ምንጭ፡ www.howstuffworks
@Abelbeencreative4