🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

#ከፍተኛ_ጥንቃቄ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት (ጅዳ) ለኢትዮጵያውያን የጥን | ALIF Travel Consultant

#ከፍተኛ_ጥንቃቄ

ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት (ጅዳ) ለኢትዮጵያውያን የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።

ከትናንት ምሽት ጀምሮ ለፅህፈት ቤቱ እየደረሱ ባሉት መረጃዎች መሠረት የሳዑዲ የፀጥታ አስጠባቂ አካላት ፦

- በጄዳ ፣
- መዲና ፣
- ጂዛን እና መካ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ዜጎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ።

በዚህም ምክንያት ጉዳዩ እስኪጣራ ድረስ ኢትዮጵያውያን ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

በሳዑዲ አረቢያ በተጠቀሱት ከተሞች የምትገኙ የቲክቫህ አባላት በሙሉ የቆንስላ ጽህፈት ቤቱን የጥንቃቄ መልዕክት በአፅንኦት እንድትወስዱ፣ እራሳችሁን እንድትጠብቁ ፤ ጥንቃቄም እንድታደርጉ አደራ እንላለን።

t.me/AlifTravelConsultant
Facebook.com/AlifTravelConsultant
Instagram.com/AlifTravelConsultant