Get Mystery Box with random crypto!

የቃለ-መጠይቅ ችሎታችሁን ለማሳደግ የሚረዱ 5 ጠቃሚ ምክሮች 1. በተቻለ መጠን አለባበስን ጽዱ | ALIF Travel Consultant

የቃለ-መጠይቅ ችሎታችሁን ለማሳደግ የሚረዱ 5 ጠቃሚ ምክሮች

1. በተቻለ መጠን አለባበስን ጽዱ እና ማራኪ ማድረግ!

ከአለባበስ ማማር ጎን ለጎን ፊታችሁ ላይ የሚነበበው መልዕክት፤ ቀጣሪዎችን የሚጋብዝ መሆን ይኖርበታል። ከፍትፍቱ፤ ፊቱ አይደል ተረቱስ?

2. በደንብ ለማዳመጥ ጆሮአችሁን ስል ማድረግ!

ለቃለ-መጠይቅ አድራጊዎቻችሁ አንጀት አርስ መልስ ለመመለስ፤ ጥያቄያቸውን በጥሞና ማዳመጥ ይገባል።

3. ነጥባችሁን ልትስቱ ስለምትችሉ ብዙ አታውሩ!

ለተጠየቀው ጥያቄ ተመጣጣኝ የሆነ መልስ ብቻ ስጡ፡፡ የባጥ የቆጡን መቀባጠር፤ ቀጣሪዎች ዘንድ ግምት ያስወስድባችኋል።

4. የቋንቋ አጠቃቀማችንን ላይ ጥንቃቄ ማድረግ!

ሙያው የሚጠይቀውን ተገቢ ቃላት መጠቀም። ዘርን፣ ሀይማኖትን እና ባህልን የሚንቋሽሹ ቃላትን ከመጠቀም መቆጠብ ግድ ይላል።

5. ሥራውን በጽኑ መፈለጋችሁ፤ ባይታወቅ ይመረጣል!

ቀጣሪዎቻችሁን ለመማጸን የምትሞክሩ ከሆነ ተሸናፊ ትሆናላችሁ።

ምንጭ: ናትናኤል ሚሞሪ

ምስል : Ladders