Get Mystery Box with random crypto!

ለ ሀያ ምናምን አመት መሌ አትዮድያን መርቶ ምድርን ቻው ብሏት ሲሄድ ግዜው ሲደርስ ተሰናብቶ ፤ | ግጥም በድምፅ

ለ ሀያ ምናምን አመት መሌ አትዮድያን መርቶ
ምድርን ቻው ብሏት ሲሄድ ግዜው ሲደርስ ተሰናብቶ ፤

ቦታዬን ከጅሎ መጥቶ ማንም ሰው ልቀቅ ሳይለኝ
እኔ እንደሁ በለሁበት ነኝ።

ከዚያም ከሱ ለጥቆ ሀይልሻ እፊት ሲመጣ
መች ዘለልሁ? ልክ እንደ ፌንጣ
እኔ እንደሁ ባለሁበት ነኝ ያላንዳች መከራ ጣጣ!

ከዚያም አመት ነጎደ በፍጥነት ቀን ገሰገሰ
በተራው አብይ ነገሰ
እኔ ግን በለሁበት ነኝ ቦታዬ መች ተወረሰ ?

ባጭሩ …

ዝሆኖች ደርሰው ቢፋጩ አንደኛው አንዱን ቢንደው
አይሞቀው ልቤን አይበርደው
ማንም ሰው ደርሶ አይቀማኝ ምክትል ቦታዬን እንደው ።

(እዮብ ዘ ማርያም)

Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam