🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

አዋሽ ባንክ በቡታጅራ ከተማ 250 ሺህ ብር ወጪ በማድረግ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ወገኖች ድጋፍ | Awash Bank

አዋሽ ባንክ በቡታጅራ ከተማ 250 ሺህ ብር ወጪ በማድረግ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ወገኖች ድጋፍ አበረከተ፦
መጋቢት 21/2016 ቡታጅራ
አዋሽ ባንክ በቡታጅራ ከተማ የሚገኙ ቅርንጫፎች 1445ኛውን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ 250 ሺህ ብር ወጪ በማድረግ ድጋፍ ለሚሹ 50 ወገኖች የኢፍጣር ማዕድ(በዓይነት) እና የካሽ ድጋፍ አበርክተዋል።
ለ50 አባ ወራ/ እማ ወራዎች በነፍስ ወከፍ 25 ኪሎ ግራም የዳቦ ዱቄት፣ 5 ሊትር ዘይት ፣1 ኪሎ ግራም ቴምር እና 1,000 ብር ካሽ በድምሩ ለአንድ ቤተሰብ 5,000 ሺህ ብር ድጋፍ አበርክቷል።
የአዋሽ ባንክ ቡታጅራ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል ጎሳዬ ባንኩ በቡታጅራ ከተማ በሶስት ቅርንጫፎች በአገር አቀፍ ደግሞ 900 መቶ ቅርንጫፎችን ከፍቶ የፋይናንስ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ከዚህም በተጨማሪ በአገር አቀፍ በ41 ከተሞች 13 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ጥቃቅንና አነስተኛ ላይ ተደራጅተው ለሚሰሩ በዝቅተኛ ወለድ ብድር እየሰጠ በማቋቋምና የስራ እድል በሚፈጠርበትም መስክ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በዛሬውም ማዕድ ማጋራት ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን በመለየት ትብብር ላደረጉላቸው ለቡታጅራ ከተማ አስተዳደር እና ለከተማው ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት፣ ለቡታጅራ ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ፣ለእናት ጓዳ በጎ አድራጎት ማህበር እና ለኢልኸስ በጎ አድራጎት ድርጅት ምስጋና አቅርበዋል።
አዋሽ ባንክ በቡታጅራ ከተማ ሶስት ቅርንጫፎች ቡታጅራ እሬሻ እና እሬንዛፍ ቅርንጫፎችን ከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።በመሆኑም እነዚህ በከተማዋ የሚገኙ ቅርንጫፎች በትብብር ያዘጋጁት የኢፍጣር ማዕድ ማጋራት ነው።
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ተወካይ አቶ ወልዩ ጀማል ከተማው በበጎ ስራ እያከናወናቸው ያሉ ስራዎች አሉ በዚህ መልኩ መታገዙ በስፋት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ነው። አዋሽ ባንክ እያደረገ ያለው መልካም ስራ የሚበረታታ መሆኑንም ገልፀው ድጋፍ በተደረገላቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ተስፋነሽ አለሙ ባንኩ የአቅም ውስንነት ላለባቸው ወገኖች ያበረከተው ድጋፍ እጅግ መልካም ስራ መሆኑን ጠቁመው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የዘገበው የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።