Get Mystery Box with random crypto!

በየቱም ግልምጫ፣ ፈኑ ሳይገፈፍ በየቱም መገፋት፣ ሃሌው ሳይሸረፍ ይሄ ፍስሀዬ፣ ፀሐይ ከመሰለ ይሄ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

በየቱም ግልምጫ፣ ፈኑ ሳይገፈፍ
በየቱም መገፋት፣ ሃሌው ሳይሸረፍ
ይሄ ፍስሀዬ፣ ፀሐይ ከመሰለ
ይሄ ፈገግታዬ፣ ኮኮብ ከመሰለ፣
ሸር እየበጠሰ
ኩርፊያ ፀብ ጥላቻን፣ እየገረሰሰ
ከእኩይ ገድ ላይ ሳቄ ሳቅ ከጫረ
(እንዲሁ እንዳማረ)

አትጠራጠሪ
ስስቅ የነበረው ሳቅሽን ነበረ።

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19