🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

​​ሳጥናኤል ቀፈፈው የመለእክት አለቃ ሳጥናኤል ሲባረር ፥ ሰው የመሆን ፈቃድ እምላክ ሰጥቶት ነበ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

​​ሳጥናኤል ቀፈፈው

የመለእክት አለቃ ሳጥናኤል ሲባረር ፥
ሰው የመሆን ፈቃድ እምላክ ሰጥቶት ነበር ፥
ሳጥናኤል ግን ከፋው ፥
ሰው መሆን ቀፈፈው ፥
ጌታን ተማፀነ ፥
ሰው አንዳያደርገው አልቅሶ ለመነ ።

ከመንበሩ ቀርቦ ሞገተ ፈጣሪን ፥
ከፍጥረትህ ሁሉ ሰው በጣም ይከፈል ፤
ይሄንን አልችልም ሰውነት ይቀፋል ፤
ሞቶስ መቼ ያርፋል ?
የሃጥያቱ ዘር ዘመን ይሻገራል ፤
ፍጹም አይማርም አዳኙን ይክዳል ፣
ስሞ ይሸጠዋል ፣ ሰቅሎ ይገድለዋል ፤
ጥበብ አጥሮት እንጂ ሰይጣንን ያስንቃል ።

እባክህ አምላኬ ፥ እኔም ፍጥረትህ ነኝ ፥
ሃጥያቴ በዝቶ ምን ብዳፈርህም ፥
ሰው የመሆን ቅጣት አትጥልብኝም ፥
ብሎ ተቀመጠ ሳጥናኤል ቆረጠ ፥
ሰው መሆንን ጠልቶ ሰይጣንን መረጠ ።

ያሬድ ዘ. ካህን
መሰከረም -12 / 2014

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19