🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

•••☆《ኑረናል እንዴ》☆••• ሚኪያስ እንዳለው @mikiendialem መርዶ ባናስነግር ሙሾ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

•••☆《ኑረናል እንዴ》☆•••
ሚኪያስ እንዳለው
@mikiendialem


መርዶ ባናስነግር ሙሾ ባናወጣም በገዛ ራሳችን፤
እንደ እውር ቢያረገን ባይነዛ ፍሬው ድካም እትብታችን፤
ግና መጠየቅ አይጎዳ ከሽሽት ለራቀው ለኔ፤
በላዬ ላይ ቢጠምቅብኝ ፍርኸት ላጠቃው ወኔ፤
የመጠየቄን እውነት በመልስሽ ድጎ ብፍልግ፤
ለውሳኔዬ ረቂቅ መጠየቅ ከሆነ ፈለግ፤
እንጂ እኛ ኑረናል ብዬ መልስ ማሰስ ልፋቴ እንዲሆነኝ፤
ተራው ደርሶ ለኔ እናም እስክጠየቅ ላሁን ጠያቂ ነኝ።

ምነው ኑሮ ማለት?
ሞትን መፍራት!
ወይስ ከተፈጥሮ ጋር መጋባት፤
ብቻ መመለስ እንደ ህልም ሲያልሙት የሚያድር፤
በህልም እልም አለም ገብቶ የሚሰወር፤
በአንድ ቃና ፍቺ የማይደረደር፤
የአንዱ ህይወት ሰሙ
ለሌላው እንደወርቅ በላዩ ላይ ሚያምር፤
"ሁሉም በአካሄዱ ትርጉም ይሰጡታል
በዝብርቅርቅ አለም አንድ ከየት ይመጣል"
ንጹህ ያልናት አለም በሌላው ውሎ አዳር ቆሻሻ ይላታል።
ላንግባባ ከንቱ ልዩነቱ ነግሶ በላያችን ሲነድ፤
አንድነቱ ጠፍቶ የመተሳሰሪያው
ቃሉ ከአንደበት ፈርቶ እንደጉድ ሲርድ፤
መጠየቁ አይከፋም ለመስማት አንዳንዴ፤
ምላሹ ካላችሁ ግን ኑረናል እንዴ!።


19-06-2013

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19