🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ና የሚሰማኝን ብታውቂው? እኔኮ በዓይኔ ነው ያየሁሽ። የምጠይቅሽ ጥያቄ አልነበረኝም። ራስሽን ይቅር | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ና የሚሰማኝን ብታውቂው? እኔኮ በዓይኔ ነው ያየሁሽ። የምጠይቅሽ ጥያቄ አልነበረኝም። ራስሽን ይቅር ያላልሽው አንቺ ነሽ። እኔ ገና ድሮ ይቅር ብዬሽ አልፌዋለሁ።"

"ምን ያህል ጊዜያችሁ ነው?"

"ካወቅኳት?" በጭንቅላቴ ንቅናቄ 'አዎ' አልኩት

"ከተዋወቅን ስድስት ወር ገደማ። .......ስለፍቅር ማውራት ከጀመርን አንድ ወር .......ከሳምኳት ሁለት ሳምንት ......." ከዛስ የሚለውን አይኔን አፍጥጬ እጠብቀዋለሁ።

"አድርገን አናውቅም። ታምኚኛለሽ?"
'አዎን' አልኩት በጭንቅላቴ ንቅናቄ:: ..... ዝም ተባባልን!! ..... ወርጄ አጠገቡ ተቀመጥኩ:: .... ምን እያሰበ እንደሆነ ልጠይቀው እፈልጋለሁ:: ግን ከአፌ አይወጣልኝም:: አቅፎ ትከሻው ላይ አስደገፈኝ:: ዝም ተባብለን ብዙ ከቆየን በኃላ ... .... አቅጣጫውን ቀይሮ ከፊቴ ተቀመጠ:: በጣቶቹ አገጬን ደግፎ ቀና አድርጎኝ አይኖቹን አይኖቼ ውስጥ ዘፍዝፎ

"ፍቅሬ እኔ ስላበድኩልሽ ያላንቺ ፍላጎት የራሴ አድርጌ ላቆይሽ እንደማልችል አውቃለሁ:: ምንድነው የምትፈልጊው? መለያየት ከሆነ የምትፈልጊው am ready now. ቢከብደኝም ልለቅሽ ዝግጁ ነኝ!! ምንድነው የምትፈልጊው? እንደገና መሞከር ነው የምትፈልጊው? Am ready ... አሁን ግን እኔን ወይም ቤተሰብሽን ሳይሆን ራስሽን ሰምተሽ ራስሽ ወስኚ .. .... የፈለግሽውን ጊዜ ያህል ውሰጂ የሚያስቸኩለኝ ጉዳይ የለብኝም::" አለኝ

"እሷስ?" (ኤጭ ዛሬ ምንድነው ችግሬ የማስበውን የማወራው?)

"(ሳቅ አለ) እሷ ስላንቺ ታውቃለች ጣጣዬን እስክጨርስ ላለመገናኘት ተስማምተናል::"

"ለመወሰን ብዙ ጊዜ ቢፈጅብኝስ?"

"10 ዓመት ጠብቄሽ የለ? እጠብቅሻለሁ::" አለኝ:: ከጀርባዬ መጥቶ እግሮቹ መሃከል አድርጎኝ ካቀፈኝ በኃላ "ያ የሚያስጠላሽንም ነገር አናደርግም (ድክም ብሎ እየሳቀ) ሆ ሰው ፍሰሃ ያስጠላዋል? (ቡፍ ካለ በኃላ) ራስሽ ፈልገሽ ያውም 'እባክህ ፍቅሬ' ካላልሽኝ አናደርግም" ብሎኝ እጁን በቱታዬ ስር ሰዶ ወገቤን አቀፈኝ::

ይሄ ሰውዬ ዛሬውኑ እባክህ ሊያስብለኝ ነው እንዴ?

#Meri feleke

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19