Get Mystery Box with random crypto!

•••☆《እነ አድር ባይ ቤቱ》☆••• ሚኪያስ እንዳለው @mikiendialem እጣረሰው ት | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

•••☆《እነ አድር ባይ ቤቱ》☆•••

ሚኪያስ እንዳለው
@mikiendialem


እጣረሰው ትዕዛዝ
አሻፈረኝ ስለው ጌታው ቁጣ አስነሳ፤
ጭራሽ ዱላ አንስቶ
እኔን ሊደበድብ በንዴት አገሳ፤

.
ይቅርታ ይቅርታ
መማፀን አበዛሁ፤
እሱን ጌታ አክብሬ
ሎሌነትን ገዛሁ፤
ድል መንሳቱ ህልሜን
በሽንፈት ነሳው፤

.
ሲፈጠር ከሀረጉ
ለገዢነት ብቻ የተፈጠረ አለ፤
እንደኔ አይነት ደሞ
ከቅባቱ ስለ'ት ሎሌ የሆነ አለ፤
ብቻ በየፊናው
ጀብደኛ እና አሽቃባጭ ፈር እየጠረገ፤
እድሜውን ይኖራል
ለሌላው አሲይዞ ጥግ እየፈለገ፤

.
መረታት ተፅፎ
ለሞቀለት ሁሉ የሚያሸረግደው፤
ለይምሰሉ ውጦት
ሰው መሆኑን ካደው።

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19