Get Mystery Box with random crypto!

ከራስ ጋር ግብ ግብ ሲያመነታ የኖረዉ አመለኛዉ ልቤ ሲኮራ የኖረዉ በተራዉ ሀሳቤ ለዚ አ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ከራስ ጋር ግብ ግብ


ሲያመነታ የኖረዉ
አመለኛዉ ልቤ
ሲኮራ የኖረዉ
በተራዉ ሀሳቤ
ለዚ አመዳሙ
ስግብግቡ አለም
ሲነግስ ሲንሸራተት
የተሾመ የለም....
ልቅር ወይስ ልሂድ
ልማለድ ልቀጣ
ለየቱ በደሌ...
ለየትኛዉ ጣጣ
ከራስ ጋር ግብግብ
......................
ከራስ ጋር ትንቅንቅ
ከሱ ሳይማከር...
ሲኖር ሀሳብ ሲንቅ
ሽምግልና ቆመ
ሰዎችን ሊያስማማ
ከቀልቡ ከልቡ
ከሱ ሳይስማማ
የሚያወሩት ሁሉ
ምጸት እየመሰለዉ
ሲዝት በሀሳቡ ...
በምን ልበቀለዉ
በቁጭቱ መሀል
ተስማሙ እያለ
በ ሌላኛዉ ጣቱ
ሰዉ እየሰለለ...
............
ከራስ ጋር ግብ ግብ
....................
ጥርሱን በጥርሶቹ
እያንቀራጨጨ
ጣቱን ከጣቱ ጋር
እያሙለጨለጨ
በለዉ በሚል ስሜት
አይኑን ሲያጉረጠርጥ
አያወጣዉ ነገር...
ተለክፎ በክፋት ምጥ
.................
ከራስ ጋር ግብ ግብ
.................
እንዴት ያለ ነገር
ይዛችኋል ሰዎች
ሽምግልና ቆመን
ሆናቹ ነዉረኞች
በል አንተም ተዉ
አንቺም ተረጋጊ
ደርሶ ቦግ ማለት
ቦልተኛ ነዉ ብለዉ
ሳይዛበቱበት
የጸብ መነሻ
ሆነና የበላይ
ፍታት ብሎ ....
ሄደ የዶሴዉ
ማብቂያ ላይ...
በ ፊፊ የተጻፈ

ቅኔ ራስ ግጥም
ከማረኮት ያጋሩ

t.me/sengomgn

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19