Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም በያላችሁበት ይብዛ እስኪ ካነበብኩት ላጋራችሁ መቼም ለመኖር ሲባል የማይኮን የለም፤ ለመማ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ሰላም በያላችሁበት ይብዛ እስኪ ካነበብኩት ላጋራችሁ

መቼም ለመኖር ሲባል የማይኮን የለም፤ ለመማር ሲል ረዥም ርቀቶች እየተጓዘ
የቤት ውስጥ ዕቃዎች በየመንደሩ የሚሸጥ አንድ ወጣት ነበር።
አንድ ቀን ውኃ ጠምቶት ወደ አንድ ቤት ተጠጋና በሩን አንኳኳ። እዚያም ፀጉሯ
ረዥም ፣ ጥርሶቿ የሚያምሩ ትንሽዬ ልጅ በሩን ከፈተችለት እናም "እባክሽ
የምጠጣው ውኃ ስጪኝ"አላት
ልጅት በወጣቱ ሁኔታ አዝና ወተት አመጣችለት። ወተቱን ከጠጣ በኋሏ"ስንት
ነው መክፈል ያለብኝ?" ብሎ ጠየቃት፤ ልጅቷ ግን ማታ ማታ ከምትጠጣው ቀንሳ
እንደሰጠችው ክፍያም እንደማያስፈልግ ነገራው፤ እሱም አመስግኗት መንገዱን
ቀጠለ።
ከጊዜያት በኋላ አንድ ቀን ልጅት ክፍል ውስጥ ራሷን ስታ ትወድቃለች
በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሀኪም ቤትም መምህራኖቿ ወሰዷት።ሀኪም ቤቱም
የልጅቷ ሁኔታ ከአቅማቸው በላይ ስለነበር። ከፍ ወዳለ ከተማ ውስጥ ወደሚገኝ
ትልቅ ሆስፒታል በፍጥነት ተወሰደች እና ህክምና ተደረገላት።
እናም ልጅቷ ራሷን ስታውቅ፤ ራሷን የከተማው ትልቅ ሆስፒታል ውስጥ ተኝታ
አገኘች። እና ጤናዋ በፍጥነት ከቀን ወደቀን ለውጥ በማሳየቱ ሆስፒታል
መቆየቷ ጥቅም ስለሌለው ሀኪሞቹ ወደ ቤቷ እንድትመለስ ወሰኑ።
ይሄኔ ልጅትና የልጅቷ ቤተሰቦች የክፍያዉን ነገር እንዴት እንደሚወጡ ኃሳብ
ገባቸውና ክፍያው ስንት እንደሆነ ሲጠይቁ እንዲህ የሚል ወረቀት ተሰጣቸው
"ከረዥም ዓመታት በፊት ለውኃ ጥም ተብሎ በተሰጠ በአንድ ብርጭቆ ወተት
ሒሳብ ተጣጥቷል"
*
በውኃ ለመናት ወተት ሰጠቺው፤ በክፍያ እንዲያክማት ብትጠይቀው በነጻ
አዳናት... ይሄ መኖር ነው።
"መልካምነት መልሶ ይከፍላል፤ ውለታ መላሽ ያድርገን"
*

እናንተ በሱ ወይም በእሷ ቦታ ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር?

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19