Get Mystery Box with random crypto!

ነገር ሲበላሽ . ወንዙ ይንጫጫን ድንጋይ ያፏጫል ካንቺ ጀርባ ጋር ገምቦ ይጋጫል ከፍ ትያለሽ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ነገር ሲበላሽ
.
ወንዙ ይንጫጫን
ድንጋይ ያፏጫል
ካንቺ ጀርባ ጋር
ገምቦ ይጋጫል
ከፍ ትያለሽ
ውሃው ይፈሳል
ሊያውም በጀርባሽ
ቁልቁል ይወርዳል(2×)
ዳሌሽ ስር ቆመ
ወዴት ይሄዳል
የራሰው ቀሚስ
ልቤን ያስከዳል
ከገላሽ ጠብቆ
ባይቆይ ደብቆ
ብስል ዱባማ የተከፈለ
የዳር መሃሉ ጠቆር ቆር ያለ
የ'ናትሽን እጅ አሻራ ያዘለ
ያሻራው ታሪክ...
የሆነ ቀን ነው
አንቺ ፅንስ ሆነሽ
እሳቸው እርጉዝ
ሸቷቸው መብል
ዳሌ ስትይዝ
እንዲ ውብ ሆነው ተወለድሽ አሉ
ፀየም እንዳለ የዳር መሃሉ
የተከፈለ ዱባ ያክላሉ

ይሄን እያሰብኩ እኔ ከኋላሽ
የጀርባሽ ገንቦ
ደልቶት ተኝቷል ነገር ሲበላሽ።

ነገር ሲበላሽ
መቅናት ስጀምር
አየሁ መቀነት
አንቺና ገንቦን የሚያስተሳስር
ግራው ወደ ቀኝ
ቀኙ ከ ግራ የተጠለፈ
በ እንስራው አንገት ታክኮ ያለፈ።
ጡቶሽ መሃል
ግራውን በ'ዚ ቀኙን ወደዛ
ወጥሮ ይይዛል
ከኋላሽ ሆኜም ነገር ሲበላሽ
ጫፉ ይታያል
እሱም ያፈዛል።

ነገር ሲበላሽ
አንቺ ስትሄጂ እኔ ስከተል
ይታወቀኛል ባስብ ስበከል
ለካስ ወንድ ሆኜ ሽመል ይዣለሁ
ዳሌሽ ጠልፎኛል
ጡጥሽ ጠልፎኛል
ይቅርታ አርጊልኝ እጠልፍሻለሁ

[ቶማስ ትግስቱ]

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19