🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

. ቦታው እንጂ : የጠፋብን ሚጣራበት ሊጎትተን ሊያስጨንቀን : 'ቁሙ' ብሎ የሚልበት እንጂማ አለ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

.

ቦታው እንጂ : የጠፋብን ሚጣራበት
ሊጎትተን ሊያስጨንቀን : 'ቁሙ' ብሎ የሚልበት
እንጂማ አለ...
በአንዱ አካል ውስጥ ተሸጉጦ
ተስፋን አንቆ ህልምን ሽጦ

ለሚያየን ሰው
ቁንጅና አለን ውብ ሆነናል
በስስት መልክ አጓጉተናል
ኮከብ መስለን አብርተናል
ግን ችግሩ... ቀዝቅዘናል

...ጎደሎ ነን
ከቶ አናውቅም ሙሉ ሆነን
አናስታውስ አንረሳ
አንወስን አንምታታ
አንጠቅም አንጎዳ
ለደስታ ሩቅ ላዘን ባዳ

ሆዳችንን
አቅፈን ይዘን : አልቅሰናል
ስቅስቅ ብለን : ሳቅ ስቀናል
ሙሉነትን አልመናል
ግን ጎለናል
ቀዝቅዘናል

መሳቅ ስንችል ሚያስተክዘን
መሮጥ ስንችል የሚጠልፈን
መዳን ስንችል የሚያደክመን
...ነገር አለን
መኖር ስንችል የሚገለን
መቆም ስንችል የሚሰብረን
መብረር ስንችል የሚያዝለን
ልንረዳው ያስቸገረን
ልንሸከም የከበደን
ከሆነ ጥግ የቋጠረን
ያረጀማ አንድ ነፍስ አለን...

ያረጀ ነፍስ ምን አይነት ይሆን??

መነሻ ሀሳብ - እሱባለው አበራ ንጉሤ
(ትዝታሽን ለኔ ትዝታዬ ላንቺ
ገፅ 89 - ልብ የላትም)

በአቤኒ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19