🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

አንችዬ ደርበብ _ ገርበብ ገረፍ በአይን ጠለፍ፣ ፍልቅ ጥርሶችሽ ፍቅ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አንችዬ

ደርበብ _ ገርበብ
ገረፍ
በአይን ጠለፍ፣
ፍልቅ
ጥርሶችሽ ፍቅልቅ
አካላቴም እልቅ
ልቤ ዋትቶ ጭንቅ፣

አንቺዬ....

ተቀብተሽ ቡራቡሬ እንሾሽላ
በንቅሳት መህተቧን አንጠልጥላ፣

አይኔም ግልጥ
ልቤም ጭልጥ፣

በሷ ዓለም......

አንችዬ......

ባለ ውቅራቷ
ባለ ንቅሳቷ፣
ሎጋ ሰውነቷ
ብርቅ ብርቅርቅነቷ፣

አንችዬ.....

የአንገት ጌጤ የኔ
ፅድቅና ኩነኔ
ልምጣ ባንቺ ዓለም
ይህ ዓለም ለምኔ።

አንችዬ.....


ሌማቷ : እንክት : ሲል : ተመልክታ: ያዘነች : ጡቷ : እንደ : ቋያ : ሳር : የድርቀት : ጠኔ : ያጠወለገው : ምድሪቱ ቁሬማ : ሆና : ስታምፅ : አዬ አልፋና ኦሜጋ : ወዴት : ነህ?

ይህ እንደሆነ የሷ አለም አደለም!


ቅዱስ አርዮስ
የግማሽ አለም ጣኦት

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19