የደጋ በረከት . ሲራክ ወንድሙ @siraaq . የተስፋ ሀገር ወዲያ ፥ የሀሳብ ሀገር ወዲህ ፣ ፋኖሱ ተሰዷል ፥ ሊመሽ ነው እንግዲህ ፤ ዶሮ ከቆጥ ሰፍሮ ፥ ሊኮኩል ሲቀጥር ፣ ይሄንን እያየ ፥ ልቤ ሲለኝ ጠርጥር ፣ በምናልባት መናጥ ፥ የቀን ድግግሞሽ ፣ እንዳሞራው ፍጥነት ፥ አክናፍ እሽክርክሮሽ ፤ ከቀየዋ ሳልሄድ ፥ በሯም ሳይዘጋ ፣ አድማስ ሲደማምን ፥ ምሽት ሲዘረጋ ፣ ባዶ እጄን ወጣለሁ ፥ ውብ አይኗን ፍለጋ። ____°°° ___ የደጋ በረከት መስከረም ፳፻፲፬ ዓ.ም ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19 1.8K viewsAbela, 08:34