Get Mystery Box with random crypto!

ገላዬ.... ከመስኩ ላይ ቆሜ ፥ እምባን ባረገዘ በናፍቆት ወይቦ ፥ በተድበዘበዘ በዚያ መንታ አይኔ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ገላዬ....
ከመስኩ ላይ ቆሜ ፥ እምባን ባረገዘ
በናፍቆት ወይቦ ፥ በተድበዘበዘ
በዚያ መንታ አይኔ...
የመራቤን ጅራፍ ፥ የምኞቴን ጩኸት
ላንቀላፋው ጤዛ ፥ ለወፍ ጎጆው ምልዓት
ዘምሬ
ዘምሬ
ደስኩሬ
ደስኩሬ
ህቅ ባለው መንፈስ ፥ ምሬት ባየው ልሳን
ብናገር ለእነሱ ፥ የኔን እንዲህ መሆን
የአንቺ ወዲያ መቅረት ፥ የንጋት ሰቀቀን
በጉድ ወጣ እያሉ ፥ ለሰማይ ለምድሩ
ለሰው ላራዊቱ ፥ ለቀየው መንደሩ
መስቀሉ ናት ብለው ፥ ናፍቆት ወለፈንዴ
ተሸነፈ ብለው ፥ ያሙኝ ይሆን እንዴ?
.................. / / .....................
ሲራክ ወንድሙ