Get Mystery Box with random crypto!

ለምትናፍቂኝ ዉድሽ ባንቺ ምክንያት ይጠጣል ይላሉ አስረዳኝ እባክህ ጉዳዩን በሙሉ ብለሽ ስትጠይቂ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ለምትናፍቂኝ

ዉድሽ ባንቺ ምክንያት ይጠጣል ይላሉ
አስረዳኝ እባክህ ጉዳዩን በሙሉ

ብለሽ ስትጠይቂኝ...........

ከአመታት ጅረት
ከሰአታት ንጉደት
ከወራት መቃዠት
ከለታት መዋተት
ከልቤ ቆጣሪዉ
ከነፍሴ ዠዋሪዉ
ከሴኮንዶች እርቃን
ከፍቅርሽ ምርቃን
ላታነቂኝ ደርሰሽ
እባክህ ንገረኝ አልሺኝ አለሳልሰሽ።

የትኛዉን ልንገር...............

አጓደኞችሽ ጋር መጥተሽ ለጫወታ
ኑ ተቀላቀሉ ስትይ በፈገግታ
ከራስሽ ቀላቅለሽ ልቤ ገራገሩን
እዉን እሱን መስማት ትሻለሽ አሁኑን?

ወይስ...........

ለሁሉም ለምኑም የመጀመሪያዬ
ወዳንቺ ሳቀና የገነት መግቢያዬ
ካንቺ ጋር ስቀመጥ ከመላዕክት ዜማ ያማረ ቃልሽን
ስሰማ መኖሬን መስማት ትሻለሽን።

የተቀመጥሽበት የተቀመጥኩበት የፍቅራችን ወንበር
ማርያምን እላለሁ ይህን እዉነት ያዉቅ ነበር።

ዉድሽ ባንቺ ምክንያት ይጠጣል ይላሉ
አስረዳኝ እባክህ ጉዳዩን በሙሉ
ብለሽ ስትጠይቂኝ..............

በነዛ ለሊቶች ያወራናቸዉን
መለያየት ተስኖን ያወጋናቸዉን
መልሼ እያሰብኩ ከዶርሜ ገብቼ
ስኖር እንደነበር ልንገርሽ አዉጥቼ።

ከመዉደድሽ ጥላ
ከኩርፊያና ሳቅሽ ተቀምጬ ኋላ
ካንቺ ተሳስሬ
መስካሪ ባላየዉ በፍቅርሽ ታስሬ።

ዉል ባልታሰረለት መፍቻ በሌለዉ ጉድ
ገርጃፋ አድርገሽዉ ልቤ አንቺን በመዉደድ።

እሱን ብነግር ይሁን ላንቺ የተሻለ
በፍቅርሽ ቀይደሽ ነፍሴ እንደዋለለ።

አረ........እዲያ መዉደዴ
ይልቅ ይቅር በይኝ
ዛሬም እኮራለሁ አንቺን በመዉደዴ።

ዉድሽ ባንቺ ምክንያት ይጠጣል ይላሉ
አስረዳኝ እባክህ ጉዳዩን በሙሉ
ብለሽ ስትጠይቂኝ..............

አፍቃሪዉ እዉሩ አይኔ ተሸፍኖ
ማጣት አይኑ ይጥፋ ብሎ አመሳክሮልኝ

ሞኙ ጅሉ ልቤ ካንቺ ሲዉል ጊዜ
ካንቺ ሲያድር ጊዜ
ልክ እንደ አሁኑ ካንቺ ሲኖር ጊዜ
ሚያጣሽ አልመሰለዉ መዉደዱን መናገር
ማፍቀሩን መመስከር ከቶ መች መጣለት
አንቺ ደረሽና እንለያይ ብለሽ መርዶ አረዳሽለት።

ፅልመቱን ህይወቴን ያኔ እንደጠራሽዉ
መኖሬን ከመሞት እንዳወዛገብሽዉ
ባወራ ይሻል ሆይ ዉዴ እንደሰማሽዉ
አስቀይመሀኛል በቃ እንለያይ ብለሽኝ እንዳልሽዉ


ብዬ ብልሽ ይሁን የጥያቄሽ መልሱ
6 አመት በፊት ካሳየሽ በስሱ

እንጃልኝ መዉደዴ
ዛሬም እኮራለሁ አንቺን በመዉደዴ።

ይልቅ ይቅር በይኝ ፍቅርሽን በደልኩ
አንቺን ልርሳ ብዬ ሌላ ሴት አቀፍኩ
ያቺኛዋን ሳምኩ
ከዛች ተጋደምኩ
ዉዴ...ዉዴ አንቺን ለመርሳት ያልሆንኩትን ሆንኩ።

ዉድሽ ባንቺ ምክንያት ይጠጣል ይላሉ
አስረዳኝ እባክህ ጉዳዩን በሙሉ
ብለሽ ስትጠይቂኝ..............

መጠጣቴ እኮ ነዉ ደፍሬ እንድደዉል ካንቺ የሚያረገኝ
ከአመታት ኋላ ድምፅሽን ሚያሰማኝ

ይገርምሻል ፂዬ ከድምፅሽ ሚወጡት የቃላትሽ ዜማ
ያስደነግጡኛል እዉነት ስልሽማ።

እንጃልኝ መዉደዴ
ዛሬም እኮራለሁ አንቺን በመዉደዴ

ዉድሽ ባንቺ ምክንያት ይጠጣል ይላሉ
አስረዳኝ እባክህ ጉዳዩን በሙሉ
ብለሽ ስትጠይቂኝ..............

ከጊዜያት ቀመር
ከሂወቴ ቁማር
አኬሩ ቢወጣ
የኛ መለያየት ሚስጢሩ ሲወጣ
ስትነግሪኝ ጊዜ
ካለፈ በዋላ የፍቅር ደሞዜ

ለካ ሀይማኖት ነዉ
ይገርምሻል ፂዬ
ከንለያይ ይልቅ ያመመኝ ይሄ ነዉ

አይኔ አነባልሽ
ዉስጤ አለቀሰልሽ
ምነዉ በነገርሺኝ
ያኔ እንዲ ነዉ ብለሽ ፂዬ ባረዳሽኝ

አሁን ይበልጡኑ እጅጉን ጎዳሽኝ
ገላዬ ቢቆሽሽ
ዉስጤ ቢቃጠልም በመጠጥ ሰክሬ

ተማሪዉ ልቤ ነዉ ዛሬም የሚወድሽ
ከሀዋሳ ካምፓስ ይድረስልኝ ፍቅሬ።


የስንታየሁ100% እዉነተኛ ታሪክ

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@TIZITA21

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19