Get Mystery Box with random crypto!

እንደቀድሞ ቢሆን... አያቴ ሲነግረኝ ድሮ በነሱ ጊዜ መጥበስ እንዲ ነበር በፍቅር አዋዜ እሚቀጣ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

እንደቀድሞ ቢሆን...

አያቴ ሲነግረኝ ድሮ በነሱ ጊዜ
መጥበስ እንዲ ነበር በፍቅር አዋዜ

እሚቀጣጠሩት ሆቴል አልነበረም
እገበያው ዘንዳ እንዳቀሪ አልቀርም

ተባብለው አውግተው
ለቀጣይ ቀጠሮ ይዘው ተለያይተው

በዛኛው ቀጠሮ እስከሚገናኙ አያወጉም ነበር
ምክንያቱም እነሱ ቃል ያከብሩ ነበር

እንደዘንድሮ ፍቅር እዩኝም አይሉም
በልብ ብቻ ነበር መውደድም ማፍቀርም

እንዲህ እንዲያ እያለ ይህን ሁሉ ሲነግረኝ
ያለንበት ዘመን እንደቀድሞ እንዲሆን እጅጉን ፈለኩኝ

ብዙ ሳናወራ ተግባብቶ መፋቀር
ሠወቹ ሳያቁ እኔን ከአንተ ጋር አንድ ላይ ማዋቀር

እንዲህ ቢሆንልኝ ነው የኔ ምኞቴ
ማንም ሳያቅብኝ ማስገባት በቤቴ

ሐና ይመር

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19