Get Mystery Box with random crypto!

ተረት ተረት ኩራትና መዉደድ ሲኖሩ ሲኖሩ 1ፍቅር እንግዛ ብለዉ ተማከሩ በዚ ሀሳባቸዉ ሁለቱም | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ተረት ተረት

ኩራትና መዉደድ ሲኖሩ ሲኖሩ
1ፍቅር እንግዛ ብለዉ ተማከሩ

በዚ ሀሳባቸዉ ሁለቱም ተስማምተዉ
1ፍቅር ገዙ ፀንተዉ በቃላቸዉ

ከለታት አንድ ቀን የሸመቷት ፍቅር
ገና ብትወጣ ከሁለቱም በልጣ
መዉደድ ተሸንፎ ከሷ ተዋደደ
ኩራትም በነሱ እጅግ ተናደደ።

ፉክክር ገጠሙ..........
በዚ ፀብ መሀል ግን ሁለቱም ታመሙ

ፍቅር ከበፊቱ እጅግ ቀዘቀዘ
ኩራትም ኩራቱ እየተናወዘ
መዉደድ ይሉት ነገር ለብቻ ከተመ
ሁሉም በየፊናዉ መራራቅ ወሰነ።

ተረቴን መልሱ ከፈለጋችሁ አትመልሱ


መጀመሪያ አካባቢ ያሉት ድሮ አማርኛ መፅሀፍ ላይ ካነበብኩት የአፃፃፍ መንገድ
በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita_wolde

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19