Get Mystery Box with random crypto!

እሳት : ነው : አልጋዬ : ግሎ : አያቃጥለም፣ ሽፋን : ያልኩት : በሬም : ከጅብ : አያስጥልም | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

እሳት : ነው : አልጋዬ : ግሎ : አያቃጥለም፣
ሽፋን : ያልኩት : በሬም : ከጅብ : አያስጥልም፣
ወገቤን : ለእሳት : አይኔን : ወደ : በሩ፣
አማትሬ : ሳድር : እነማን : ነበሩ?
እጄስ : መቼ : ያርፋል፣
እየቃዠም : ቢሆን : አፌ : ይለፈልፋል፣
እግሬም : ባይራመድም : እየጠዘጠዘኝ፣
ሳይመቸኝ : እየኖርኩ : ስቃዬ : አመለጠኝ፣
የመኖር ፡ ቤት ፡ ሁኜ ፡ ሞት ፡ ጎርብቶ ፡ እያየሁ፣
ወይ ፡ እረፋት ፡ አልሆነኝ ፡ ወይ ፡ አልተሰቃየሁ፡፡

ናታን ኤርሚያስ
@UniqueDy

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19